የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዓመት የጽ/መሳሪያ፣ የፅዳት እቃ፣ የተለያዩ ህትመቶች፣ የመብራት ዕቃ፣ ዉሃ እቃዎች፣ የቢሮ ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የመኪና ጎማ እና የኦክሲጅን ሙሌት ማሽን ጥገናን በ9 ሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።
የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል 1. የጽ/መሳሪያ 2. የፅዳት እቃ 3. የተለያዩ ህትመቶች 4. የመብራት ዕቃ 5. ዉሃ እቃዎች 6. የቢሮ መገልገያ እቃዎች /ፈርኒቸሮች/ 7. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 8. የመኪና ጎማ ከነ ከመናዳሪ 9. የኦክስጅን ሙሌት ከነማጓጓዣ እና ጫኝና አውራጅን ጨምሮ የኦክስጅን ሲሊንደር አጠቃላይ ጥገና ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት -
በዘመኑ / 2019 በጀት ዓመት /የታደሰ ወይም አዲስ የወጣ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ። የግዥ መጠኑ 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሆስፒታሉ የእለት ገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ከዚህ በታች በተመለከተው ሰንጠረዥ መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታሉ ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ የተከፈለበትን ደረሰኝ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አብረው አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
| ተ.ቁ | ሎት | የግዥው አይነት | የጨረታ ሰነድ መሸጫ ብር | የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን |
|---|---|---|---|---|
| 1 | ሎት-1 | የጽ/መሳሪያ | 200 | 40,000 |
| 2 | ሎት-2 | የፅዳት እቃ | 200 | 25,000 |
| 3 | ሎት-4 | የተለያዩ ህትመቶች | 200 | 20,000 |
| 4 | ሎት-5 | የመብራት ዕቃ | 200 | 35,000 |
| 5 | ሎት-6 | ዉሃ እቃዎች | 200 | 35,000 |
| 6 | ሎት-7 | የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች /ፈርኒቸሮች/ | 200 | 20,000 |
| 7 | ሎት-8 | ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች | 200 | 50,000 |
| 8 | ሎት-9 | የመኪና ጎማ | 200 | 25,000 |
| 9 | ሎት-11 | የኦክስጅን ሙሌት ከነማጓጓዣ እና ጫኝና አውራጅን ጨምሮ የኦክስጅን ሲሊንደር አጠቃላይ ጥገና | 200 | 40,000 |
- ተጫራቾች ከአሸነፉ በኋላ ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ፣ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን 4:00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ማስገባት ይችላሉ። የጨረታ ሳጥኑ ወዲያዉኑ ይታሸጋል በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰአት ይከፈታል። በአላት ቀን ከሆነ በቀጣይ ስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል።
- የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ40ቀን ፀንቶ ይቆያል።
- ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት በስልክ ቁጥር 0116813390 ወይም በፋክስ 0116811008 ቁጥር በመላክ መጠየቅ ይቻላል።
(ስለ ናሙና፣ ጥራትና ርክክብ ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎች በጋዜጣው ላይ ተገልጸዋል።)
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሠረዝ መብቱ እንዲሁም ግዥውን በጥቅል ወይም በተናጠል አወዳድሮ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
