የሸካ ዞን ማሻ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች ቀለብ የሚውል እህል፣ ጥራጥሬና ሸቀጣ-ሸቀጥ ከታህሳስ 1 እስከ መጋቢት 30/2019 ዓ.ም ለ120 ቀናት እንዲሁም የ2019 በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።
የሸካ ዞን ማሻ ማረሚያ ተቋም
የጨረታ ማስታወቂያ
ለሸካ ዞን ማሻ ማረሚያ ተቋም በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ቀለብ እህል ጥራጥሬ እና ሸቀጣ-ሸቀጥ ከታህሳስ 1/2019 ዓ.ም እስከ መጋቢት 30/2019 ዓ.ም ለ120 ቀናት እና የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያ ከሚያቀርቡ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸዉ ድርጅቶች ፣አቅራቢ ነጋዴዎችና ማህበራት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸዉ ግዴታዎች:-
1ኛ/ በየዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸዉና የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
2ኛ / ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
3ኛ/ የጨረታዉ ተወዳዳሪዎች ለዕህል ለጨረታዉ ማስከበሪያ ብር 50000 /ሀምሳ ሺህ ብር/ እና ለሸቀጣ-ሸቀጥና ለጥራጥሬ ጨረታ ማስከበሪያ 20000/ሃያ ሽህ ብር ለጽህፈት መሣርያ ጨረታ መስከበርያ 10000/አስር ሽህ ብር በጥሬ /በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 3 የጨረታ ሰነድን መግዛት የሚችል፣
4ኛ/ ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ያለዉን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5ኛ/ ጨረታዉ በ16ኛዉ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል።
6ኛ/ ጨረታ የሚከፈትበት ቀን የመንግስት ሥራ ሰዓት ካልሆነ በሚቀጥለዉ ቀን በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ይከፈታል።
7ኛ/ የጨረታዉ አሸናፍ የሆነዉ አቅራቢ ዕቃዎችን አጓጉዞ በራሱ ወጭ ለማሻ ማ/ተቋም ማስረከብ የሚችል
8ኛ/ ተጫራቾች አሁን ባቀረቡት ዋጋ ለ4 ተከታታይ ወር ማቅረብ የሚችል ሲሆን በመሀሉ የድርድር ጥያቄ ተቀባይነት የለዉም
9 ኛ /ተጫራቾች ህጋዊ መጋዘን ስለመኖራቸዉ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል !
10ኛ/ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
