ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ የግብዓት አቅርቦትና የመስተንግዶ አገልግሎት (በድጋሚ)
Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 033/19
ድርጅታችን ለሁለት አመት የሚቆይ የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ የግብዓት አቅርቦትና የመስተንግዶ አገልግሎት በድጋሚ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ደፈልጋል ። ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 500,00 ከፍለው በመግዛት የፋይናንሺያል እና የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው ።
ጨረታው በ15/03/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰአት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አደገደድም።
ስልክ ቁጥር 011-1-55-52-30
ድረ ገፅ (www.ethbspe.org)
Berhanena selam printing enterprise
አዲስ አበባ
