የአርባምንጭ አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ማዕከል የጽህፈት፣ አላቂ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የሕንፃ፣ የህክምና ዕቃዎች፣ ማሽነሪዎች፣ ፈርኒቸርና ደንብ ልብስ ግዥ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአርባምንጭ አካል ጉዳተኞች ተሀድሶ ማዕከል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአርባምንጭ አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ በሎት 2 ሌሎች አላቂ ዕቃዎች በሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በሎት 4 የሕንፃ መሳሪያ ዕቃዎች በሎት 5 ሞተር ሳይክሎችና የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች በሎት 6 የህክምና ዕቃዎች በሎት 7 ማሽነሪዎች በሎት 8 ቆዳና የቆዳ ዉጤቶች በሎት 9 ፈርኒቸር በሎት 10 ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል:- ስለሆነም መ/ቤታችን ጨረታውን የሚያከናወነዉ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅና የግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሠረት በግልጽ ጨረታ ሆኖ ለውድድሩ የሚጋበዙ ተጫራቾች
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸዉ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/Tin Number/ ያላቸዉ እና ከ200,000 ሺ.ሀ ብር በላይ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል:
- ለህክምና ዕቃዎች በኢ.ት/ያ የህክምና ዕቃዎች አስተዳደር ቁጥጥር ባለሥልጣን የህክምና ዕቃዎች የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የተዘጋጀዉን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 /አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ 100.00/አንድ መቶ/ ብር በመክፈል ከአርባምንጭ አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ማዕከል ቢሮ ቁጥር የጨረታዉን ሠነድ በመግዛት እስከ 15ኛው ቀን 11:30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሠነዱን መወሰድ ይችላሉ:
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ 5000.00/ አምስት ሺህ/ ብር በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /cpo/ ማስያዝ አለባቸዉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸዉን መ/ቤቱ በሸጠላቸዉ የጨረታ ሠነድ ላይ የአንዱን ዋጋ በሚለዉ ቦታ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ ዋጋ በመሙላት ኦርጂናልና ኮፒ ላይ ፊርማቸዉን እና የድርጅታቸዉን ማህተብ በማድረግ በታሸገ ኢንቨሎፕ ዉስጥ ለዚሁ የተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸዉ፤
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቀን ለ15/አሥራ አምስት ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛዉ ቀን የጨረታው ሣጥን ከጥዋቱ 4:00 ሰዓት በማስገባት ወዲያዉኑ ታሽጎ በዚያዉ ቀን ከጥዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በማዕከሉ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፤ 16ኛዉ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ይከፈታል በጨረታዉ መከፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ያለመገኘት የጨረታዉን መከፈቻ አያስተጓጉልም:
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈዉን ዕቃ እስከ ማዕከሉ የማምጣትና የማቅረብ ግዴታ አለበት። አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች የተጫረቱትን ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸዉ.
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ። ይህ ሲባል ጨረታዉ በመሰረዙ ተጫራቾች ለጨረታ ዉድድር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነት አይወስድም
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 0468810564 /0468814168/ ይደውሉ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአርባምንጭ አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ማዕከል
✨ messages.ai_summary
Arba Minch Rehabilitation Center for Persons with Disabilities seeks suppliers in 10 lots: stationery, consumables, electronics, building materials, motorcycles and spare parts, medical items, machinery, leather, furniture and uniforms.
