Tender Detail

Tender Details


የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉና ለማኅበረሰብ መድሀኒት ቤት የሚውሉ መድኃኒቶች፣ የላቦራቶሪ ሪኤጀንቶች፣ ሜዲካል ስፕላይ፣ የህክምና መሳሪያ፣ መለዋወጫ እቃዎችና ኮስሞቲክስ ለአንድ ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።

የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አጠቃላይ የውስጥ ፋርማሲ አገልግሎት እና ለማኅበረሰብ መድሀኒት ቤት አገልግሎት የሚውል መድኃኒት፣ የላቦራቶሪ ሪኤጀንት፣ሜዲካል ስፕላይ ፣ የህክምና መሳሪያ ፣ መለዋወጫ እቃዎች እና ኮስሞቲክስ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት:-

  • በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር እንዲሁም የኢትዮጵያ የምግብና የመድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደር የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦሪጅናሉንና ኮፒ በጥንቃቄ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፣
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን መድኃኒት፣ የላቦራቶሪ ሪኤጀንት፣ ሜዲካል ስፕላይ ፣የህክምና መሳሪያ ፣ መለዋወጫ እቃዎች እና ኮስሞቲክስ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን መድኃኒት፣ የላቦራቶሪ ሪኤጀንት ፣ሜዲካል ስፕላይ ፣የህክምና መሳሪያ ፣ መለዋወጫ እቃዎች እና ኮስሞቲክስ በሆስፒታሉ የጨረታ ሰነድ አይነትና ዝርዝር /ስፔስፊኬሽን/ መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር/ ማስያዝ አለባቸው። (አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።)
  • ተጫራቾች ከአሸነፉ በኋላ የሚያሲዙት የጨረታ ውል ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ከሆነ የግዜ ቆይታው 12 ወር መሆን አለበት።
  • ተጫራቾች የአሸነፉትን መድሃኒት ለተከታታይ ሶስት ግዜ ታዘው ካላቀረቡ ያሲያዙት የውል ማስከበሪያ ተወርሶ ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል።
  • ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ10 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን 4:00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ማስገባት ይችላሉ። የጨረታ ሳጥኑ 4:00 ይታሸጋል በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል። 11ኛው ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል።
  • የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ40 ቀን ፀንቶ ይቆያል።
  • ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት፣ በስልክ ቁጥር 0116813390 ወይም 0116376994 በፋክስ 0116811008 ቁጥር በመላክ መጠየቅ ይቻላል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሠረዝ መብቱ እንዲሁም ግዥውን በጥቅል ወይም በተናጠል የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

(ስለ አቅርቦት፣ ጥራትና ዋጋ ማቅረቢያ ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎች በጋዜጣው ላይ ተገልጸዋል።)

የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

✨ messages.ai_summary
Debre Berhan Comprehensive Specialized Hospital (Amhara) buys medicines, laboratory reagents, medical supplies, medical equipment, spare parts and cosmetics for one year for its pharmacy and community pharmacy. Licensed suppliers with EFDA competence certificates may bid.
Save Tender