Tender Detail

Tender Details


በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ፣ የህክምና፣ የትምህርትና የጽዳት እቃዎች፣ ልዩ ልዩ እቃዎች፣ የህንፃ ህድሳት እቃዎች፣ ቋሚ እቃ እና የሽልማት እቃዎችን በ9 ዓይነት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የቡልቡላ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥ ጨረታ:-

  1. 6211 የደንብ ልብስ
  2. 6212 አላቂ የቢሮ እቃ
  3. 6214 አላቂ የህክምና እቃ
  4. 6215 አላቂ የትምህርት እቃ
  5. 6218 አላቂ የጽዳት እቃ
  6. 6219 ልዩ ልዩ እቃዎች
  7. 6244 የህንፃ ህድሳት እቃዎች
  8. 6313 ቋሚ እቃ
  9. 6417 የሽልማት እቃ ናቸው

በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የዘመኑ ግብር የከፈሉበት የቫት ከፋይ ሰርተፍኬት በገንዘብና በኢኮኖሚ ልማት ሚንስቴር መስሪያ ቤቶች የእቃና አገልግሎት ግዥ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ
  2. የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ለጨረታውን (ሲፒኦ) ማቅረብ የሚችሉ። ሲፒኦውም
    2.1. 6211 የድንብ ልብስ 40,000/አርባ ሺ. ብር/
    2.2. 6212 አላቂ የቢሮ እቃ 15,000/አስራ አምስት ሺ. ብር/
    2.3. 6214 አላቂ የህክምና እቃ 5,000/አምስት ሺ./
    2.4. 6215 አላቂ የትምህርት እቃ 40,000/አርባ ሺ. ብር/
    2.5. 6218 አላቂ የጽዳት እቃ 15,000/አስራ አምስት ሺ. ብር/
    2.6. 6219 ልዩ ልዩ እቃዎች 15,000/አስራ አምስት ሺ. ብር/
    2.7. 6244 ለህንፃ ህድሳት እቃዎች 4,000/አራት ሺ. ብር/
    2.8. 6313 ቋሚ እቃ 50,000/ሃምሳ ሺ. ብር/
    2.9. 6417 የሽልማት እቃ 5,000/አምስት ሺ. ብር/ ነው
  3. ከላይ ለተዘረዘሩ እቃዎች ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ጨረታውን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከት/ቤቱ ፋ/ ቢሮ ቁጥር 4 በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በግልጽ በመሙላትና ፊርማ ማህተም በማድረግ በኤንቨሎፕ በማሸግ ዋናውንና ኮፒውን ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 5 ማስገባት አለባቸው።
  5. ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ይሆናል።
  6. ማንኛውም ተጫራች ለተጠየቃቸው እቃ ሁሉ ናሙና ማቅረብ ግዴታ ይኖርበታል።
  7. ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት በ11 ቀን ላይ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይዘጋና በዛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  8. በጨረታው ሂደት ቅሬታ ያለው አካል ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ እስከ 3 ቀን ድረስ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል።
  9. የጨረታው አሸናፊ ላሸነፈው እቃ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መዋዋል ግዴታ ሲሆን አልዋዋልም ቢል ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  10. ተጫራቾች ባቀረቡት ናሙና መሰረት አሸናፊ ሲሆኑ ያሸነፉበት እቃ በናሙናው መሰረት ማቅረብ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ካላቀረቡ በህግ ይጠየቃሉ።
  11. ተጫራቾች አስቀድ ባለ እቃ መወዳደር ሲኖርባቸው እቃው ገበያ ላይ የለም ወይም ዋጋ ጨምሯል በሚል ሰበብ አልዋዋልም በሚሉ ተጫራቾች ላይ ት/ቤቱ አግባብ ባለው ህግ መሰረት የሚጠይቃቸው ይሆናል።
  12. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ 011 442 60 36 መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ:- ሳሪስ ሬስ ኢንጅነሪንግ ጀርባ

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የቡልቡላ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Bulbula General Secondary School (Akaki Kality Sub-City, Addis Ababa) buys uniforms, office, medical, educational and cleaning supplies, miscellaneous items, building renovation materials, fixed assets and award items. Registered suppliers with renewed licence and VAT; samples required.
Save Tender