የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር ዕቃዎች፣ ሞተር ሳይክሎችና የሞተር ሳይክል ጎማ ግዥ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 07/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለጉራጌ ዞን ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት አንድ....የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- ሎት ሁለት....የተለያዩ ፈርኒቸር ዕቃዎች፣
- ሎት ሶስት.....የተለያዩ ሞተር ሳይክሎችና የሞተር ሳይክል ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታዉ መወዳደር ትችላላችሁ :-
- ተጫራቾች ህጋዊና የዘመኑ የታደሰ ወይም አዲስ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የታክስ ከፋይነት መለያ ቁጥር/TIN/ ያላቸው፣
- የአቅራቢነት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግዢዉ መጠን ከብር 500,000/ አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱት እና የሚመለከታቸዉ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻቸዉ ሰነድ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እቃ አይነት፣ የአምራቹን ስምና የተመረተበት ዓ.ም በዝርዝር ከዋናዉ ሰነድ ጋር ማያያዝ አለባቸዉ።
- ለሚወዳደሩባቸዉ እቃዎች ናሙና ሲጠየቁ ማቅረብ አለባቸዉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1 ብር 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ/፣ ለሎት 2 ብር 100,000/ አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ/ እና ለሎት 3 ብር 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም ቢድ ቦንድ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም ተዘጋጅቶ ከኦርጂናል ዶክመንት ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት የማይመለስ ለእያንዳንዳቸዉ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ ለጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ በመክፈል ሰነዱን ከጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት እስከ 15ኛዉ ቀን ከቀኑ 11:30 ሰዓት ድረስ ብቻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ሲያቀርቡ ለፋይናንሺያል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ በሰም በማሸግ /ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ እስከ 16ኛው ቀን 8:00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ዕለት ከቀኑ 8:30 ሰዓት የጨረታ ሰነድ ያለበትን ሳጥን ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል።
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ እንደተገለፀለት በውሉ መሠረት ዕቃዎቹን ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ:-
ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ 90 ቀንና ከዚያ በላይ የሚቆይ መሆን አለበት።
ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0113300112 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፣
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፤
ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
✨ messages.ai_summary
Gurage Zone Finance Department seeks suppliers for zone sector offices in 3 lots: electronic items, furniture, and motorcycles with motorcycle tyres. Open bid.
