Tender Detail

Tender Details


የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሚሊሻ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዴስክቶፕ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ላፕቶፕ፣ LCD ፕሮጀክተር እና የኤሌክትሪክ ሞተርሳይክል በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሚልሻ ጽ/ቤት


ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሚሊሻ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ማለትም ዴስክቶፕ ኮፒውተር፣ፕሪንተር፣ላፕቶፕ፣ LC.D.ፕሮጀክተር እና የኤሌክትሪክ ሞተርሳይክል በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት

  1. በግብር ከፋይነት ተመዝግበው የአቅራቢነት ሠርተፍኬት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆነው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በጨረታ መሳተፍ የሚችሉበትን የግዜ ገደብ የሚገልፅ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማስረጃ በመያዝ ለያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ)ብር በመክፈል ሰነድ በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ተከታታይ ቀናት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሚሊሻ ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ የውል ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በማዘጋጀት ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታ መመሪያ ጋር አባሪ ተደርጎ ይያያዛል።
  3. ይህ ጨረታ በ16ኛው በሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ታሽጎ ከ4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 16ኛው ቀን ቅዳሜና ዕሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ የጨረታ መክፈቻ ዕለት በተጠቀሰው ሰዓት በሚቀጥለው ሥራ ቀን ይሆናል።
  4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ስምና አድራሻ በግልፅ በመሙላት በማህተምና በፊርማ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ። አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ።
  5. ተጫራቾች መመሪያ ባለማክበራቸው የሚፈፀም ማንኛውም ስህተት ኃላፊነቱ የተጫራቾች ይሆናል።
  6. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ:- ሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፊት ለፊት ትንሽ አለፍ ተብሎ ባለው ግቢ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 5

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሚልሻ ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር .0462124273

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሚልሻ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Sidama Region Militia Office (Hawassa) buys office electronics, namely desktop computers, printers, laptops and LCD projectors, plus an electric motorcycle, by national open tender. Registered suppliers with TIN, VAT and paid taxes may bid.
Save Tender