Tender Detail

Tender Details

  • Company በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የፊታውራሪ አባይነህ መተኪያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ከጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል በስተቀኝ በኩል ባለው ደብረ ዘይት መንገድ አዲስ የተሰራው ድልድይ ላይ 200 ሜ ወደ ግራ ታጥፎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-11-93-95-47
  • Website
  • Deadline26 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 200.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityሎት1 30,537.22፤ ሎት2 30,000፤ ሎት3 1,000፤ ሎት4 28,000፤ ሎት5 8,000፤ ሎት6 8,960.68፤ ሎት7 16,000 ብር (CPO፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
  • opening dateበዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:30
  • Categories Furniture And Furnishing , Cleaning And Janitorial Equipment , Medical Equipment And Supplies , Stationery Materials , Cloth And Shoes , Educational And Training Equipment And Machinery

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የፊታውራሪ አባይነህ መተኪያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት፣ የህክምና፣ የትምህርት፣ የጽዳት፣ ልዩ ልዩና ቋሚ ዕቃዎች ግዥ

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የፊታውራሪ አባይነህ መተኪያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የፊታውራሪ አባይነህ መተኪያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 የበጀት ዓመት1ኛ ዙር ጥቅል ግዥ ግልጽ ጨረታ በመፈፀም በስራ ላይ የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ፈልጋል:-

  • ሎት 1. 6211 የሠራተኛ ደንብ ልብስ 2% ማስያዝ የሚጠበቅባቸው .......................30,537.22
  • ሎት 2. 6212 የጽህፈት መገልገያ ቢሮ ዕቃዎች 2% ማስያዝ የሚጠበቅባቸው.....30,000
  • ሎት 3. 6214 አላቂ የህክምና ዕቃዎች 2% ማስያዝ የሚጠበቅባቸው.......................1,000
  • ሎት 4. 6215 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች 2% ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ..................28,000
  • ሎት 5. 6218 አላቂ የጽዳት መገልገያ ዕቃዎች 2% ማስያዝ የሚጠበቅባቸው............8,000
  • ሎት 6. 6219 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች 2% ማስያዝ የሚጠበቅባቸው.................................8,960.68
  • ሎት 7 6313 ቋሚ ዕቃዎች 2% ማስያዝ የሚጠበቅባቸው .................................16,000

በዚሁ መሰረት በግልጽ ጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ሟሟላት የሚገባችሁ:-

  1. በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ።
  2. ተጫራቾች በዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለበት።
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ቫትን ጨምሮ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው መሙላት አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ከየዓይነቱ አንድ አንድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታው ውጤት ከታወቀ በኋላ ያቀረቡት ናሙናዎች ለተሸናፊዎች ሲመለስ የአሸናፊዎቹ ተጫራቾች ናሙና ግን አይመለስም።
  7. ግዥ ፈፃሚው አካል ለአሸናፊ ተጫራቾች በሚመረጡበት ጊዜ የሚገዛውን ዕቃ ወይም የአገልግሎት መጠን እንደ አስፈላጊነቱ 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃዎች ናሙና ወይም ሳምፕል ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም ተጫራቾች በምታቀርቡት ናሙና /ሳምፕል ላይ ምንም ዓይነት ማህተም፣ስልክ ቁጥር እና ሌሎች ምልክቶችን ማድረግ ከውድድር ውጪ ያደርጋል።
  9. የጨረታ ማስከበሪያ በመሙላት ጠቅላላ ዋጋ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በገንዘብ ተወሰ[...] በየሎቱ በተጠቀሰው መሰረት ሲፒኦ /cpo/ ፊታውራሪ አባይነህ መተኪያ አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት በሚል ለስራው አመቺነት ሲባል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ በተዘጋጀ ሲፒኦ (CPO) በማሰራት በዋናው ወይም በኦርጂናል ሠነድ ውስጥ ማቅረብ አለባቸው።
  10. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሠዓት በት/ቤቱ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 07 ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር ብቻ) የማይመለስ በመክፈል የጨረታውን ሠነድ መግዛት ይችላሉ ።
  11. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሠነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ በመሙላት በመጨረሻ ቦታ ላይ ስም፤ ፊርማና ህጋዊ ማህተም በማኖር በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት ከ2:30 -11:00 ሠዓት ዋጋቸውን በመሙላት በተጠቀሰው የሥራ ሠዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሠዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 ይከፈታል የተጫራቾች ወይንም የወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም ።
  12. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተረጋገጠ በኋላ በሚጫረቱት የጨረታ ዋጋ ላይ በመመስረት የሚመለስ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/cpo/ ማስያዝ አለባቸው።
  13. አሸናፊ ተጫራቾች በራሱ (በተጫራቹ) ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  14. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆንና ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ይወረስባቸዋል።
  15. መስሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
  16. ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በሚያመርቱት ዕቃ ላይ የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ከሚያመርቱት ዕቃ ውጪ ከሆነ በደብዳቤ መስተናገድ አይችሉም ።
  • አድራሻችን:- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ከጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል በስተቀኝ በኩል ባለው ደብረ ዘይት መንገድ አዲስ የተሰራው ድልድይ ላይ 20 ሜ ወደ ግራ ታጥፎ ነው። ፊታውራሪ አባይነህ መተኪያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
  • ለበለጠ መረጃ :- በስልክ ቁጥር 0911-93-95-47 ወይም 0911-74-51-13

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የፊታውራሪ አባይነህ መተኪያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Fitawrari Abaineh Metekiya General Secondary School (Akaki Kality, Addis Ababa) seeks suppliers in 7 lots: staff uniforms, stationery, medical, educational and cleaning consumables, various tools and fixed assets. Open bid.
Save Tender