Tender Detail

Tender Details


የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከኒሳ ጤና ጣቢያ የቋሚ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቢሮ፣ የጽዳት፣ የጥገና እቃዎች፣ ህትመትና የጉልበት ስራ ግዥ

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 ከኒሳ ጤና ጣቢያ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ በከኒሳ ጤና ጣቢያ 2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎች በግዥ መለያ 001/2019 ማለትም በሎት 1 ቋሚ እቃዎች በሎት 2 የጥገና እቃዎች ሎት 3 አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት 4 አላቂ የጽዳት እቃዎች ሎት 5 ህትመቶች ሎት 6 የጥገና እቃዎች እና 8 የጉልበት ስራ ሌሎችም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም:-

ሎት ቁጥርየጨረታ አይነትየጨረታ ማስከበሪያ የብር መጠንምርምራ
ሎት 1ቋሚ እቃዎች30000
ሎት 2ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች30000
ሎት 3አላቂ የቢሮ እቃዎች15000
ሎት 4ደንብ ልብስ1000
ሎት 5አላቂ የጽዳት እቃዎች5000
ሎት 6የጥገና እቃዎች5000
ሎት 7ህትመቶች10000
ሎት 8የጉልበት ስራ5000

በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት:-

  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ የአቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 300 (ሶስትመቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነዱን ጤና ጣቢያ ፋይናንስ ቢሮ ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
  3. የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛ ቀን እስከ 11:30 ሰዓት ድረስ አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት በጤና ጣቢያው መሰብሰቢያ አዳራሽ ጨረታው ይከፈታል። ነገር ግን የጨረታው መከፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን በተባለው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ሙሉውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ጤና ጣቢያው ግቢ ውስጥ ግዥ ቡድን ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት የመ/ቤቱ ፍላጎት (ስፔስፍኬሽን) ለሚያስፈልጋቸው ሎቶች በጥንቃቄ በስፔስፍኬሽኑ መሰረት ብቻ መሞላት አለበት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ሎቶች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል ።
  7. የዘገየ ጨረታና የጨረታ መከፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ የተቀባይነት የለውም ።
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  9. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ በከኒሳ ጤና ጣቢያ ወረዳ 02 ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር 09-96-94-34-34

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ በከኒሳ ጤና ጣቢያ

✨ messages.ai_summary
Kenisa Health Center (Nifas Silk Lafto Sub-City, Woreda 02) seeks suppliers in 8 lots: fixed assets, electronics, office and cleaning consumables, uniforms, maintenance items, printing and labour work. Open bid.
Save Tender