በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምሥ/ጎጃም ዞን የሸበል በረንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ የስራ ክፍል በወረዳው ዉስጥ ለሚገኙ ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት1:- የጽ/መሳሪያ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የሸበል በረንታ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ 01/2019
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምሥ/ጎጃም ዞን የሸበል በረንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ የስራ ክፍል በወረዳው ዉስጥ ለሚገኙ ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት1:- የጽ/መሳሪያ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።
- የተሰጣቸው የንግድ ስራ ፈቃድ 1 ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው፣ የቲን ናምበር /የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ ቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የቫት ሰርተፍኬት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ክሊራንስ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና የግዥው መጠን ከ ብር 500000.00/አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ ከፋይነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ሁሉም የእቃ አቅርቦት ተወዳዳሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃወችን በመያዝ ሰነድ ሲገዙ ሲመጡ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የእቃ አቅርቦት ስራዉን ሙሉ በሙሉ በራሱ አቅርቦት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን የቴክኒካል ሰነዶችንና የጨረታ ማስከበሪያ በአንድ ፖስታ፣ ፋይናንሽያል የያዘ ሰነዶችን በአንድ ፖስታ ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድ ማጠቃለያ ፖስታ በጥንቃቄ አሽገዉና ማህተም አድርገዉ ማቅረብ አለባቸው።
- እያንዳንዱ ተጫራች ሰነዱን የሚያሟሉት በነጻ የገበያ ዋጋ ላይ ተመስርቶ መሆን አለበት። ለሞሉትም ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት1:- 34000.00 /ሰላሳ አራት ሺህ ብር/ ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም (Bid Bond) እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ከማጠቃለያ ፖስታዉ ጋር ለብቻዉ በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሰው ስራ የጽሁፍ ማመልከቻ በማቅረብ ለሎት1 የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 09 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ይህ ማስታወቂያ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለዕቃ ግዥ ለ10 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ በ11ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን 4:00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል። ዕለቱ የበዓል ቀን/ዝግ/ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል ። ጨረታው በሚከፈትበት ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት የማያስቀር መሆኑን እንገልፃለን።
- አቅርቦቱን ለማቅረብ ውል ከተፈራረምንበት ቀን ጀምሮ ለጽ/መሳሪያ እቃዎች በገቡት ውል መሰረት በ20 ተከታይ ቀናት ማጠናቀቅ ይኖርበታል። ሆኖም ከአሸነፉበት ዋጋ የዋጋ ልዩነት ቢኖር ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ የማናደርግ መሆኑን እንገልጻለን።
- በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም አይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸዉ።
- የተጫራቾች የመጫረቻ ድጋፍ ሰነዶቻቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን አለበት።
- አሸናፊዉ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ ውል ማስከበሪያ የሚሆን ለዕቃ ግዥ 10% ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም (Bid Bond) እና ባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በማስያዝ ዉል መያዝ ይኖርባቸዋል።
- ለሁሉም ተወዳዳሪዎች የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ለእቃ አቅርቦት 45 /አርባ አምስት ቀናት/ እንዲሁም ለተጨማሪ 28 /ሃያ ስምንት ቀናት/ መሆኑን መገንዘብ አለበት።
- በጨረታ መሙያ ዝርዝር ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካደረጉ ከጨረታ ውድድር ውጭ የሚሆን ሲሆን ተጫራቾች መመሪያ በሶፍት ኮፒ መውሰድ ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0582470509 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የሸበል በረንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ የሥራ ክፍል
የዕድውኃ
✨ messages.ai_summary
Shebel Berenta Woreda Finance Office (East Gojjam, Amhara) invites bids to supply stationery items for sector offices in the woreda. Open bid.
