አዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ እና ያገለገሉ እቃዎች፣ ብረታ ብረቶችና የህክምና እቃዎች ሽያጭ
Adama Hospital Medical College (የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
አዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት:-
1. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ለሁለተኛ ጊዜ ለመግዛት፤
2. የተለያዩ ያገለገሉ/አሮጌ እቃዎች፤ ብረታ ብረቶች፤ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የህክምና ዕቃዎች ለአንደኛ ጊዜ ለመሸጥ በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ።
- የ2018/19 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ በዘርፉ ያላችሁ፤
- ተጫራቾች የተጨመሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆኑ መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸሁን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ ገዥ መ/ቤት ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦሪጅናል ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማሸግ አለባቸው፤
- ስርዝ ድልዝ ያለው፤ የማይታይ የጨረታ ሰነድ/የዋጋ ዝርዝር እና እስፔስፍኬሽን የቀየረ ተቀባይት የለውም፤
- ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ዋጋ 10% ማስያዝ የሚችል፤
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 1ኛ ላይ ላለው ተራ ቁጥር ጨረታ 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ አለባቸው፤
- ያገለገሉ/አሮጌ እቃዎች ምትጫረቱ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኮሌጁ ንብረት እና አስተዳደር ክፍል በአካል በመምጣት እቃዎቹን መመልከትና መጫረት ይችላሉ፤
- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጨረታው የሚከፈተው በ18/03/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ተጫራቾች / ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ያገለገሉ/አሮጌ እቃዎች፤ ብረታ ብረቶች፤ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የህክምና እቃዎች ጨረታው የሚከፈተው በ17/03/2019 ከጠዋቱ 4:00 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ በመስሪያ ቤቱ ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት።
ጨረታ ማስከበሪያ:-
* 1ኛ ላይ ላለው ተራ ቁጥር 50,000 (ሃምሳ ሺ) ብር በ "CBE, CBO እና በSinqe" ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
* 2ኛ ላይ ላለው ተራ ቁጥር 50,000 (ሃምሳ ሺ) ብር በካሽ ማስያዝ አለባቸው።
* ያገለገሉ/አሮጌ እቃዎች፤ ብረታ ብረቶች፤ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የህክምና እቃዎች ያሸነፈው ተጫራች በተከታታይ 5 (አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ እቃዎቹን ማንሳት እንዳለበት እያሳወቅን ይህ ካልሆነ ግን ያሲያዘው ብር ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ ሌላ ጨረታ የሚወጣ ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ
✨ messages.ai_summary
Adama Hospital Medical College is buying various electronics (second round) and selling used items, scrap metals, used electronics and medical items (first round) by open bid.
