የባሕርዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት በዳንግላ ከተማ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት የሐራጅ ሽያጭ
የባህርዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
አፈ/ ከሳሽ እነ ይነገስ አለሙ 2 ሰዎች አፈ/ተከሳሽ ህዊት ያሲን
መካከል ስላለው የአፈፃፀም ከስ ክርክር ጉዳይ በወ/ሮ ህዊት ያሲን ስም የተመዘገበውን በዳንግላ ከተማ አስተዳደር 05 ቀበሌ በምስራቅ የቦታ ቁጥር 121፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ክፍት ቦታ፣ በደቡብ የቦታ ቁጥር 122 መካከል ተወስኖ የሚገኘውን በ150 ካ.ሜ ቦታ ላይ የተሰራ የመኖሪያ ቤት ግምት ብር 1,188,645.58 /አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሰማኒያ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ አርባ አምስት ብር ከሀምሳ ስምንት ሳንቲም/ ፣የዶርም ቤት ግምት ብር 308,725.89 /ሶስት መቶ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ አምስት ብር ከሰማኒያ ዘጠኝ ሳንቲም/ እና የቦታ ግምት ብር 262,500 /ሁለት መቶ ስልሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/ በአጠቃላይ የመነሻ ዋጋ ብር 1,759,871,47 አንድ ማሊዮን ሰባት መቶ ሀምሳ ዘጠኝ ሺህ ስምንት መቶ ሰባ አንድ ብር ከአርባ ሰባት ሳንቲም/ ሆኖ በ10/04/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00-6:00 ሰዓት ድረስ በግልፅ ጨረታ ስለሚሸጥ መጫረት የምትፈልጉ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ መኖሪያ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ በሰዓቱና በቦታው በመገኘት ተመዝግባችሁ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበትን 1/4ኛውን በሞ/85 በፀደይ ባንክ ወዲያውኑ ማስያዝ የሚጠበቅበት መሆኑን ፍ/ቤቱ አዟል።
