Tender Detail

Tender Details

  • Company National Insurance Company of Ethiopia S.C (ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ)
  • Address ላንቻ ባቡር ጣቢያ ፊት ለፊት ዘፍኮ ሕንፃ በሚገኘው በዋናው መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 8 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-466-11-29
  • Websitehttps://niceinsurance-et.com/
  • Deadline28 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 200.00 (የማይመለስ)
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateበዕለቱ ጠዋት በ4:30 ሰዓት፣ የኩባንያው የንብረት ማከማቻ ግቢ
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Vehicle

ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ከዕዳና ዕገዳ ነፃ የሆኑ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ ዕቃዎች እና ሌሎች ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

National Insurance Company of Ethiopia S.C (ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ)


የተጎዱ ተሽከርካሪዎችና የተሽከርካሪዎች ቅሪት አካላት እና ሌሎች ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ጨረታ
የጨረታ ቁጥር 07/26

ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ከዕዳና ዕገዳ ነፃ የሆኑ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ ዕቃዎች እና ሌሎች ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች ከህዳር 7 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ከህዳር 19 ቀን 2019 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ንብረቶቹን ከህዳር 7 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ከህዳር 19 ቀን 2019 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ድረስ ከሃና ማርያም ወደ ቃሊቲ አደባባይ በሚወስደው ቀለበት መንገድ ከቻይና ጠጠር መፍጫ ፊት ለፊት በስተግራ በኩል የአጠና መሸጫ አጠገብ ከሚገኘው የኩባንያው የንብረት ማከማቻ መጋዘን ውስጥ በአካል ተገኝተው መመልከት ይችላሉ።
  3. የጨረታ መነሻ ዋጋው 15% ተ.እ.ታ ያላካተተ ወይም ያልጨመረ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ተ.እ.ታ ሳይጨምሩ በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) ወይም በእንግሊዝኛ NATIONAL INSURANCE CO. OF ETHIOPIA (S.C.) ስም በማንኛውም ባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ጋር በኤንቬሎፕ በማሸግ ከህዳር 7 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ከህዳር 19 ቀን 2019 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ላንቻ ባቡር ጣቢያ ፊት ለፊት ዘፍኮ ሕንፃ በሚገኘው በዋናው መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 8 በሚገኘው የሰው ሀብትና ፋሲሊቲ ሥራ አመራር መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  4. ጨረታው ህዳር 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ ጠዋት በ4:30 ሰዓት ላይ ከሃና ማርያም ወደ ቃሊቲ አደባባይ በሚወስደው ቀለበት መንገድ ከቻይና ጠጠር መፍጫ ፊት ለፊት በስተግራ በኩል የአጠና መሸጫ አጠገብ ከሚገኘው የኩባንያው የንብረት ማከማቻ ግቢ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  5. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።

ስልክ 011-470-5378/011-466-11-29

ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

✨ messages.ai_summary
National Insurance Company of Ethiopia S.C. is selling, as is, damaged vehicles, vehicle salvage parts and used office equipment taken over after insurance claim payments, by open bid.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender