ፀደይ ባንክ አ.ማ የSSL ሰርተፍኬት፣ የአይቲና የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች እና የደንብ ልብስ ግዥ
Tsedey Bank S.C. (ፀደይ ባንክ አ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/0011/2019
ፀደይ ባንክ አማ ከስር የተዘረዘሩትን ዕቃዎች/ስራዎች/አገልግሎቶች ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት ይፈልጋል።
ሎት-1 SSL Certification
ሎት- 2 የአይቲና የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች
| ተ.ቁ | የዕቃው ዓይነት | መለኪያ | ብዛት |
| 1 | Heavy duty bank note counting machine | በቁጥር | 164 |
| 2 | Medium duty note counting machine | በቁጥር | 231 |
| 3 | Switch 24 port | በቁጥር | 50 |
| 4 | Truncate 25mm*40mm | ሜትር | 900 |
| 5 | Data outlet double | በቁጥር | 250 |
| 6 | Power outlet double | በቁጥር | 500 |
| 7 | Medium duty photocopier | በቁጥር | 76 |
| 8 | Tablet computer | በቁጥር | 05 |
| 9 | Color printer | በቁጥር | 01 |
| 10 | Tag printer | በቁጥር | 13 |
| 11 | 6U Rack | በቁጥር | 50 |
| 12 | 24 port patch panel | በቁጥር | 50 |
| 13 | Webcam Camera | በቁጥር | 211 |
| 14 | Currency Detecting Machine | በቁጥር | 02 |
| 15 | Currency Detecting Marker | በቁጥር | 04 |
| 16 | Medium duty printer | በቁጥር | 159 |
| 17 | UTP cable roll | በቁጥር | 50 |
| 18 | Scanner flat bed | በቁጥር | 221 |
ሎት-3 የደንብ ልብስ
| ተ.ቁ | የዕቃው አይነት | መለኪያ | ብዛት |
| 1 | ካኪ ብትን ጨርቅ | ሜትር | 25,964 |
| 2 | የወንድ ሸሚዝ | ቁጥር | 6,625 |
| 3 | የሴት ሸሚዝ | ቁጥር | 1,971 |
ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት ነጋዴ መወዳደ የሚችል መሆኑን እንገልጻለን።
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመካፈል/ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት/ክሊራንስ ጊዜው ያላለፈበት። ቴክኒካል ዶክመንትና የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የ90 ቀን በፀደይ ባንክ አማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል። ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም ።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከህዳር 07 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ የሂሳብ ቁጥር 1201390000037 በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ ጨረታው እስከ ሚዘጋበት ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ድረስ አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ውል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በተዘጋበት ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- የጨረታው መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ :- አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ በሚገኘው የፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት ስልክ ቁጥር 0115581658
ፀደይ ባንክ
✨ messages.ai_summary
Tsedey Bank S.C. invites bids in 3 lots: SSL certification, IT and office equipment (note counters, printers, scanners, switches and more), and uniform fabric and shirts. Open bid.
