Tender Detail

Tender Details


የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ ደንብ ልብስ፣ ህትመት፣ የህክምና ኦክስጅንና የኤክስሬ ክፍል በር ግዥ

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ሞቲቴ ፉራ የመጀ/ደ ሆስፒታል


የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2019 በጀት አመት የተለያዩ አላቂ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።

በዚህ መሰረት

  • ሎት 1 - ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ
  • ሎት 2 - ፈርኒቸር ግዥ
  • ሎት 3 - የደንብ ልብስ
  • ሎት 4 - የህትመት ስራ ግዥ
  • ሎት 5 - የህክምና ኦክስጅን
  • ሎት 6 - የኤክስሬ ክፍል በር (lead)

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም

  1. ተጫራቾች በመስኩ የ2019 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ እንዲሁም የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸዉ።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፍኬት እና የታክስ ከፋይነት ቲን ቁጥር ሊኖራቸዉ ይገባል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000372939398 በመክፈል ዘዉትር በሥራ ሰአት ሞቲቴ ፉራ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በፈለቀች ሆቴል በኮብልስቶን ገባ ብሎ በሚገኘዉ ሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 39 ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የሥራ ቀናት እሁድ እና ቅዳሜን ሳይጨምር ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11:30 ከምሳ ሰአት ዉጪ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪ CPO ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ላለዉ ለእያንዳንዱ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺ ብር) ሕጋዊ ከሆነዉ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ግደታ አለባቸዉ።
  5. ተወዳዳሪዎች የሚያቀረቡትን ሰነድ ዋናውና (ፋይናንሻል) እና ፎቶ ኮፒ(ቴክኒካል)ሰነዶቹን ለየብቻ በሰም በታሸጉ ፖስታ በማሸግ ከላይ በተጠቀሰዉ ቀን እና ቢሮ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  6. ጨረታውን የሚከፈተዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8:30 ሰአት ታሽጎ በእለቱ 9:00 ሰአት ይከፈታል፡ ፡ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል ባዓል ከሆን ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታዉ ይከፈታል።
  7. የጨረታ አሸናፊ የሆነዉ አቅራቢ ድርጅት እቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት ሆስፒታል ድረስ በማምጣት የማቅረብ ግዴታ አለበት።
  8. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462200046 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የሞቲቴ ፉራ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

✨ messages.ai_summary
Motite Fura Primary Hospital (Hawassa City Administration Health Department) seeks suppliers in 6 lots: electronics, furniture, uniforms, printing, medical oxygen and an X-ray room lead door. Open bid.
Save Tender