Tender Detail

Tender Details

  • Company Ahadu Bank S.C
  • Address , Phone: 251115260796
  • Website
  • Deadline16 Dec 2026, 9:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየሐራጁ መነሻ ዋጋ 1/4ኛ (CPO፣ በአሐዱ ባንክ አ.ማ ስም)
  • opening dateNot stated in the notice
  • Sector Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

አሐዱ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣንና ውክልና መሠረት ቀጥሎ የቀረቡትን ንብረቶች በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

Ahadu Bank S.C


የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር 029/2018

አሐዱ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣንና ውክልና መሠረት ቀጥሎ የቀረቡትን ንብረቶች በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የመያዣ ሰጪ ስም አበዳሪ ቅርንጫፍ የንብረቱ አይነት አድራሻ የካርታ ቁጥር የቦታ ስፋት የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር ቀን ሰዓት ሐራጅ የወጣው
1 ሲስቲክ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ወ/ሮ ከብረቴ አለማየሁ በቀለ መስቀል አደባባይ መኖሪያ ቤት አ.አ ከተማ፣ ኮ/ቀ/ክ/ከተማ፣ ወረዳ 07 (ቤተል አለም ባንክ)፣ የንግድ ካርታ ኮርድኔት ቁጥር 9.00476.38.68176 AA000090703560 160 ካ.ሜ የሆነ (B+G+2) 47,031,220.00 ታህሳስ 7 ቀን 2019 ዓ.ም ከ3:00-4:00 ለአራተኛ ጊዜ
2 ሲስቲክ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር እነ ወ/ሮ ከብረቴ አለማየሁ (5 ሰዎች) መስቀል አደባባይ መኖሪያ ቤት አ.አ ከተማ፣ ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 07 (ቤተል አለም ባንክ)፣ የንግድ ካርታ ኮርድኔት ቁጥር 9.00344.38.68113 AA000090703347 120 ካ.ሜ ቪላ ቤት 12,180,607.00 ታህሳስ 7 ቀን 2019 ዓ.ም ከ4:00-5:00 ለአራተኛ ጊዜ
3 አልባዬ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ወ/ሮ አስቴር ሀይሉ ካሳ መስቀል አደባባይ መኖሪያ ቤት አ.አ ከተማ፣ ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 08 (ቤተል አለም ባንክ)፣ የንግድ ካርታ ኮርድኔት ቁጥር 9.013924.38.839374 AA000060802648 150 ካ.ሜ 9,895,791.00 ታህሳስ 8 ቀን 2019 ዓ.ም ከ3:00-4:00 ለ2ኛ ጊዜ

የሐራጅ ደንቦች -

  1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በአሐዱ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
  2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መክፈል አለበት። ካልተከፈለ የተያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃሉ። በጨረታው ተሸናፊ ለሆኑት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል።
  3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው ብቻ ናቸው። ተበዳሪ እና ወኪሎቻቸው ባይገኙም ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  4. የጨረታ አሸናፊ ለሆነው ተጫራች በባንኩ የብድር ፖሊሲ፣ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ መሠረት ብድር ሊመቻች ይችላል።
  5. የተጫራቾች ምዝገባ ከእያንዳንዱ ሐራጅ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል። በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም።
  6. የሐራጁ አሸናፊ ገዢ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ከስም ማዛወሪያ ክፍያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ የግብር ግዴታዎችን ገዢው አሸናፊው ይከፍላል።
  7. ተጫራቾች የጨረታው ቀን ከመድረሱ 5 (አምስት) ቀን በፊት ከባንኩ ጋር በመነጋገር በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ በቦታው በመገኘት ለጨረታ የቀረበውን ንብረት መጎብኘት ይቻላል።
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በፅሑፍ ሲደርሰው ነው።
  9. ጨረታው የሚከናወነው በአዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 08 ፍላሚንጎ ሬስቱራንት ፊት ለፊት ሰንሻይን ህንፃ ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 8ኛ ፎቅ ሐመር አዳራሽ ነው።
  10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115260223 (ሕግ አገልግሎት መምሪያ) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አሐዱ ባንክ አ.ማ

Summary
Ahadu Bank S.C. is selling by open auction three residential houses in Kolfe Keranyo Sub-City, Addis Ababa, pledged as loan collateral at its Meskel Square branch.
Not stated in the notice: opening date, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender