Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ
  • Address ከፓስተር አደባበይ 50 ሜትር ገባ ብሎ ባለው ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline24 Nov 2026, 5:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityከ0.5 እስከ 2 % 2,000 (ሁለት ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ
  • opening dateበ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 3:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • Sector Catering And Cafeteria Services

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ/ም የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ (ካፍቴሪያ) የምግብ፣ የትኩስና ለስላሳ መጠጦች አገልግሎት የሚያቀርብ ድርጅት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ያወጣው ማስታወቂያ (ቁጥር 002/2019)።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2019

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ የ2019 ዓ/ም በግልፅ ጨረታ የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ ለሰራተኞች ምግብ፤ትኩስና ለስላሳ መጠጦች አገልግሎት የሚያቀርብ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ሎት1.የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ ካፍቴሪያ አገልግሎት በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. ከላይ ከተራ ቁጥር 1- ለተጠቀሰው አገልግሎት በዘርፉ ሕጋዊና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  3. ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. ቲን ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
  5. ተጫራቾች የገዙትን መደበኛ የጨረታ ሰነድ በተጫራች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች በአግባቡ ተሞልቶና በድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ተደርጎበት ሙሉ መደበኛ ጨረታ ሰነዱ መመለስ አለበት ፡ ሰነዱን ያልመለሰ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከፓስተር አደባባይ 50 ሜትር ገባ ብሎ ባለው ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 በመገኘት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከ0.5 እስከ 2 % 2,000 (ሁለት ሺህ)ብር በባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ ከዋጋ መሙያ ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 10ኛው ቀን 11:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሰነዱን ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች እያንዳንዱን የሚሸጡበትን ነጠላ ዋጋ ከነቫቱ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ከፓስተር አደባባይ 50 ሜትር ገባ ብሎ ባለው ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  9. የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ የመጨረሻው ቀን በ10ኛው ቀን እስከ ከቀኑ 11:30 ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 3:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4ተኛ ፎቅ በጤና ጣቢያው አዳራሽ ውስጥ ይሆናል፡፡
  10. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ መድሀኒት ላይ ተቋሙ ያስቀመጠውን ዩኒት መሰረዝ፤መቀየር አይቻልም፡፡

ማሳሰቢያ-1. የምግብና የመጠጥ አገልግሎቱን ለሰራተኛው በኩፖን እየተቀበለ ቅድሚያ አገልግሎቱን ሰጥቶ የወሩ መጨረሻ ህጋዊ ደረሰኝ በማምጣት ክፍያውን ከጤና ጣቢያው ይወስዳል፡፡

  1. የተለያዩ ስብሰባዎች እና ስልጠናዎች ሲኖሩ ውሀ፤ለስላሳ፤ቆሎ እና ድፎ ዳቦ እንዲሁም ሻይ ቡና ትዛዝ ሲሰጥ ማቅረብ አለበት፡፡
  2. አሸናፊው ድርጅት ስራ ሲጀምር ጤና ጣቢያው ያስረከበውን ዕቃ በሀላፊነት መያዝ አለበት፡፡
  3. ተወዳዳሪ ድርጅት ጤና ጣቢያው ያቀረባቸውን የምግብና የመጠጥ አይነቶች ዋጋ መሙላት አለበት።ሁሉንም ካልሞላ ከውድድር ውጪ ነው የሚሆነው፡፡

ስልክ ቁጥር:- 0118-95-94-78/0930-69-56-68

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ

Summary
Felege Meles Health Center (Addis Ketema Sub-City Woreda 6, Addis Ababa) seeks a firm or individual to run its staff cafeteria, serving food, hot and soft drinks against coupons, plus refreshments for meetings. Bidders need a renewed licence, VAT and TIN.
Save Tender