Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline18 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300(ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Securityሎት 1 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 10,000.00፤ ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች 15,000.00፤ ሎት 3 ቋሚ ዕቃዎች 45,400.00፤ ሎት 4 ደንብ ልብስ 11,000.00፤ ሎት 5 መስተንግዶ 5,000.00፤ ሎት 6 የካፌ አገልግሎት 25,000.00 (በባንክ የተመሰከረለት CPO)
  • opening dateበዚያውኑ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።
  • Categories Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather , Catering And Cafeteria Services , Cleaning And Janitorial Equipment , Office And Home Furniture

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በ2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የሚያስፈልጋቸው:-የጽዳትዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ መስተንግዶ አገልግሎት የሰራተኞች ካፌ አገልግሎት ግዥን አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል::

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በ2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የሚያስፈልጋቸው:-የጽዳትዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ መስተንግዶ አገልግሎት የሰራተኞች ካፌ አገልግሎት ግዥን አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል::

በዚሁ መሰረት በጨረታ መወዳደር የሚችሉ አቅራቢዎች:-

  1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የንግድ መለያ ቁጥር TIN
  3. የዘመኑን ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉ እና ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎች ማቅረብ ሚችሉ፤
  4. የአቅራቢነት ሰርትፍኬት ያላቸው /ከአቅራቢነት ያልተወገዱ፤
  5. ቫት የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት CPO በሚያቀርቡት ገንዘብ ዋጋ:-
    ሎት የዕቃ /አገልግሎት ዓይነት በመቶኛ የጨረታማስከበሪያ ብር መጠን
    1 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 1% 10,000.00
    2 የፅዳት ዕቃዎች 1% 15,000.00
    3 ቋሚ ዕቃዎች 1% 45,400.00
    4 ደንብ ልብስ 1% 11,000.00
    5 መስተንግዶ 1% 5,000.00
    6 የካፌ አገልግሎት 1% 25,000.00
  7. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት አዲሱ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት እና እዛው ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
  8. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች በሙሉ በመሙላት በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና ማህተም በማኖረፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ከላይ ከ1- 6 የተጠቀሱትን ሰነዶች ኮፒ በአንድ ላይ ማሸግ፣ ኮፒዎቹንም ለየብቻ ማሸግ እና የቴክኒካል ሰነድ ወይም ናሙና ለማቅረብ ለማያስፈልግ ለብቻ በማሸግ በእያንዳንዱ ላይ ሙሉ አድራሻ በትክክል በመሙላት ሶስቱንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
  10. የጨረታ ሰነዱ በሙሉ የማይመለስ አቅራቢ ከጨረታው ይሰረዛል፤
  11. በጥቃቅንና አነስተኛ፣በአካል ጉዳተኞች ማህበር እና ኀጋዴ ሴቶች ማህበራት የተደራጁቹ በራሳቸው ምርት ላይ ልዩ አስተያየት ስለሚደረግ፣ የጨረታ ሰነዱንም ያለ ክፍያ እንድትወስዱ አምራች መሆናቸው፣ የመልካም ስራ አፈጻጸም መረጃ፣ፈቃዳቸን ስለላ ያልስተለለፋቹ መሆኑን የሚገልፅ መረጃ ካደራጃቸዉ አካል የድጋፍ ደብዳቤ በጽ/ቤት ኃላፊ ብቻ የተፈረመ እና የምትወዳደሩበት ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን የተጠቀሰበትን ማቅረብ አለባችሁ፤
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ጠዋት 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያውኑ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ላይ የሚከፈት ይሆናል። 11ኛው ቀን ስራ ያለበት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፤
  13. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ 2 ቀን በፊት ለሁሉም ዕቃዎቻቸው ናሙና ወይም ስፔስፊኬሽን ስለ ዕቃው በደንብ በሚገልጽ መልኩ ተዘጋጅቶ ማቅረብ መቻል አለባቸው፤ የናሙና መቀበያ ቅፅ በ2 ኮፒ አዘጋጅቶ የድርጅቱ ማህተም በማድረግ አብሮ ማቅረብ መቻል ያለባቸው ሲሆን፣ የሚቀርቡ ናሙናዎች ላይ ምንም ዓይነት ምልክትና ጽሑፍ መደረግ የለትም፤ ወይም ምልክት/ማህተም/ ጽሁፍ የተደረገበት ናሙና ወይም የናሙና መያዣ እቃዎች በቀላሉ የሚቀደዱ ከሆኑ የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን፤
  14. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ VAT ጨምሮ ያለ ስርዝ ድልዝ በትክክል መሞላት አለበት
  15. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው ከሆነ ተቀባይነት የለውም፤
  16. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ የጨረታ ውጤት ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው ቀን ውል መፈረም አለበት፤
  17. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም፤
  18. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ:- ከአውቶቢስ ተራ ወደ አጣና ተራ በሚወስደው መንገድ ሰፈረ ሰላም ኢትዮ ጤቢብ ሆስፒታል ፊትለፊት 200 ሜትር ገባ ብሎ

በአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 4 አስተዳደር አዲሱ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት የ ቢሮ ቁጥር 203፣

ስልክቁጥር:- 011-279-3338

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Addis Ketema Sub-City Woreda 4 Finance Office, Addis Ababa, buys in a second-round open tender: office consumables, cleaning items, fixed items, uniforms, hospitality service and staff cafe service (6 lots). Bidders need a renewed trade licence, TIN, tax clearance, supplier certificate and VAT.
Save Tender