Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline16 Dec 2026, 10:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityእያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል።
  • opening dateየቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
  • Sector Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የሚገኘውን የቦታ ስፋቱ 63.44 ካ/ሜ የሆነ ቤት (የይዞታ መለያ ቁጥር AA000090707739) በመነሻ ዋጋ ብር 3,241,528.32 በሐራጅ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ኲመራ ገመቹ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ሶአል አስሜኪና ላኪ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/16835 በ27/06/2018ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/23853 በ28/08/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር አዲስ የይዞታ መለያ ቁጥር AA000090707739 የሆነ የቦታው ስፋት በካርታቸው መሰረት 63.44ካ/ሜ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 3,241,528.32 ( ሶስት ሚሊዮን ሁለት መቶ አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ ሃያ ስምንት ብር ከ32/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 7 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፤ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን ፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

Summary
The Federal Courts Judgment Enforcement Office auctions by court order a house on a 63.44 sq m plot (holding no. AA000090707739) in Kolfe Keranio Sub-City Woreda 07, Addis Ababa. The auction is held in the office’s auction hall; inspection visits are arranged before the auction. Open to all bidders.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender