በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት መልካ ጉራ ቅድመ አንደኛ፣አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የጽህፈት፣ የፅዳት፣ የደንብ ልብስ እና ቋሚ እቃዎችን በ4 ሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ (መ/ጎ/ት/ቤት/03/2019)።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት መልካ ጉራ ቅድመ አንደኛ፣አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው መለያ ቁጥር መ/ጎ/ት/ቤት/03/2019
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት መልካ ጉራ ቅድመ አንደኛ፣አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
| ሎት | የግዥው ዓይነት | የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
|---|---|---|
| ሎት 1 | የጽህፈት እቃዎች | 20,000.00 (ሀያ ሺ ብር ብቻ) |
| ሎት 2 | የፅዳት እቃዎች | 20,000.00 (ሀያ ሺ ብር ብቻ) |
| ሎት 3 | የደንብ ልብስ | 20,000.00 (ሀያ ሺ ብር ብቻ) |
| ሎት 4 | ቋሚ እቃዎች | 15,000.00 (አስራ አምስት ሺ ብር ብቻ) |
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር ከፍለው ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ እና ያልታገዱ፣
- በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ እና የታደሰ የግብር ከፋይ መለያ (Tin) ቁጥር ያላቸው፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡዋቸውን እቃዎች ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁና ለዚህም ለእያንዳንዱ እቃ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር) የስራ ተከታታይ ቀናት በስራ ሰዓት አጀምባ 20 ሜትር ገባ ብሎ የመልካ ጉራ የመ/ደ/ት/ቤት 1ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ የሰነዱን መግዣ ብር የአንድ ሎት መግዣ ዋጋ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቫትን ጨምሮ በግልፅ ዋናውንና ኮፒውን በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት 1ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የሰነዱን ኮፒና ኦሪጅናል ቴክኒካልና ፋይናንሻሉን በመለየት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ህጋዊ በሆነ ባንክ ሲፒኦ(CPO) በማሰራት በየሎቱ በተጠቀሰው ዋጋ መሰረት በንግድ ዘርፋቸው ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣ በ11ኛው ቀን /03/2019ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰአት ላይ ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ይከፈታል።
- መስሪያ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ ባሉት ተከታታይ 07 (ሰባት) ቀናት ውስጥ ቅሬታ ካላቸው በደብዳቤ የማቅረቢያ ጊዜ ሲሆን የቅሬታ ጊዜ ካለፈ በኋላ በ(05) ቀን ውስጥ ውል በመቅ ቀርበው ካልተዋዋሉ የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ይሆናል፤በተጨማሪም ወደ ሁለተኛ ተጫራች የምናልፍ መሆኑን እንዲሁም ውል ሲዋዋሉ ያሸነፉበት የእቃ 10 ፐርሰንት ሲፒኦ በማስያዝ በተጨማሪም እቃውን በ15 ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3:00 እስከ 6:00 ከሰአት 7:30 እስከ 10:00 1ኛ ፎቅ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል ይህ ካልሆነ ከስራ ቀናቱ ከተጠቀሰው ሰዓት ውጪ ለሚፈጠረው መጉላላት ተጠያቂ የማንሆን መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች ናሙና በተጠየቀባቸው እቃዎች ጨረታው እስከ ሚዘጋበት እለት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ፀንቶ የሚቆየው 60 ቀን ይሆናል፤ ከበጀት አንፃር ካሸነፈው ጨረታ 20% መጨመር መቀነስ እንችላለን፡፡
- በጥቃቅንና አነስተኛ ላይ ተደራጅተው የሚሳተፉ አቅራቢዎች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ስትመጡ ካደራጃችሁ አካል በፅ/ቤቱ ሀላፊ ብቻ በስም እና በስራ ድርጅቱ የተፈረመ ቲተር ያለበት እና በእኛ አድራሻ የተፃፈ ደብዳቤ መሆን ይኖርበታል ለሚመለከተው ሁሉ ተብሎ እንዲሁም በስኪርቢቶ የተፃፈ ደብዳቤ የማንቀበል መሆኑን አውቃችሁ አሟልታችሁ መምጣት ይኖርባችኋል፡፡
አድራሻ:- በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስ/ትምህርትና ስልጠና ጽ/ቤት መልካ ጉራ ቅድመ አንደኛ፣አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
ለበለጠ መረጃ:- 09-13-81-48-49//09-20-71-39-48
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት መልካ ጉራ ቅድመ አንደኛ፣አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
Summary
Melka Gura Pre-primary, Primary and Middle School (Kolfe Keranio Sub-City, Addis Ababa) buys stationery, cleaning materials, uniforms and fixed assets in four lots. Open to registered, non-suspended suppliers with renewed trade licence, VAT and TIN; MSEs may bid.
