Tender Detail

Tender Details


በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎችና ጎማዎች ግዥ (በድጋሚ)

በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት


በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በስሩ ለሚገኙ መስሪያ ቤቶች ፈርኒቸሮች ፣ አላቂ እቃዎች ማለትም (የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች እና የተለያዩ መጠን ያላቸዉ ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ ::
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸዉን የሚገልጽ መስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ (CPO) ብቻ 100,000( አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ) በክፍለ ከተማችን ውስጥ ባሉት ባንኮች በተመሰከረ (CPO) ብቻ ማቅረብ የሚችሉ ::
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመዉሰድ በትክክል በመሙላት በታሸገ ፖስታ ዋናውና ፎቶ ኮፒዉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
  6. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን ተጫራቾች የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በስንቄ ባንክ አካዉንት ቁጥር 1064628071215 የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በማለት ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ።
  7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይንም ቅዳሜ እና እሁድ ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት እስከ 4:00 ሰነዱን የጨረታ ሳጥን ገብቶ በዚያው ቀን 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል።
  8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ጨረታዉን ከመከፈት አያግድም።
  9. ፅ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እየገለጽን ለበለጠ መረጃ የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት እቃ ግዢ ክፍል በአካል ቀርበዉ መረዳት ይችላሉ።

የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት

Summary
Sululta Sub-City Finance Office, Sheger City Administration, re-advertises an open bid for furniture, stationery, cleaning materials and tyres of various sizes for offices under it.
Save Tender