በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የተለያዩ ህትመቶችን በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በጤና ሚኒስቴር እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት በከልሉ ለሚገኙ ለክትባት ታላሚ ለሆኑ የማህበረሰብ ከፍሎች ጥራቱን የጠበቀ ክትባት በመደበኛ ፕሮግራምና በዘመቻ ተደራሽ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እነዚህን ተግባራት ለማጠናከር ከጤና ሚኒስቴር GAVIFPP(HSS-4) ለሥራ ላይ ማስተማሪያ መረጃ /Job aid እና የከትባት አሰጣጥ የግዜ ሰሌዳ /EPI schedule/ለማሳተም እና ላሚኔት ለማድረግ በተገኘ ድጋፍ የመደበኛ ከትባት መርሀ ግብር የግዜ ሰሌዳ/Routine Immunization schedule/ የማካካሻ የክትባት መርሀ ግብር የጊዜ ሰሌዳ/Catch-up vaccination schedule/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል፡፡