አፋር ጨው ማምረቻ አ/ማ አፍዴራ የሚገኘውን በአውሎ ንፋስ ምክንያት ጣራቸው የተጎዳ የጨው ማምረቻ ፋብሪካ እና የሠራተኞች መኖሪያ ሕንጻዎች ባለሞያዎችን አወዳድሮ በጨረታ ለማሰራት/ ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡
አፋር ጨው ማምረቻ አ/ማህበር አፍዴራ ለሚገኘው የጨው ማምረቻ ሳይት አጠቃላይ ስፋታቸው በግምት 40,000 /አርባ ሺ/ ስኳር ሜትር በሆኑ ክሪስታላይዜሽን ፖንዶች ውስጥ ተከማችቶ የሚገኘውን ግምቱ 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሣ ሺ) ኪዩቢክ ሜትር የጨው ምርት ቆፍሮ ከስክሶና ሰብስቦ፣ ለመጫን ዝግጁ የሚያደርግ ባክሆ ሎደር በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
አፋር ጨው ማምረቻ አ/ማሕበር በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አፍዴራ ወረዳ የጨው ፕሮሰሲንግ ፕላንት ለመገንባት የአዋጭነት ጥናት እያገባደደ የሚገኝ ሲሆን የዚህ ጥናት አካል የሚሆን የአካባቢ ተጽፅኖ ጥናት በተጓዳኝ ፍቃድ ያላቸው ባለሙያዎችን አወዳድሮ ማስጠናት ይፈልጋል፡፡