Tender Detail

Tender Details

  • Company የአፋር ጨው ማምረቻ አ/ማህበር
  • Address ሃያ ሁለት ማዞሪያ፣ አከሱም ሆቴል አጠገብ በየነ ጠበሉ ህንጻ 7ተኛ ወለል ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116187073
  • Website
  • Deadline13 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/
  • opening date2025-12-13 00:00:00
  • Categories Construction Works

አፋር ጨው ማምረቻ አ/ማ አፍዴራ የሚገኘውን በአውሎ ንፋስ ምክንያት ጣራቸው የተጎዳ የጨው ማምረቻ ፋብሪካ እና የሠራተኞች መኖሪያ ሕንጻዎች ባለሞያዎችን አወዳድሮ በጨረታ ለማሰራት/ ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡

የአፋር ጨው ማምረቻ አ/ማህበር


 

አፋር ጨው ማምረቻ አ/ማ

የጨረታ ማስታወቂያ

 

አፋር ጨው ማምረቻ አ/ማ አፍዴራ የሚገኘውን በአውሎ ንፋስ ምክንያት ጣራቸው የተጎዳ የጨው ማምረቻ ፋብሪካ እና የሠራተኞች መኖሪያ ሕንጻዎች ባለሞያዎችን አወዳድሮ በጨረታ ለማሰራት/ ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውንና የጨረታውን ማስታወቂያ፣ የተጫራቾች መመሪያ፣ የሚሰራውን ሥራ ዝርዝር የያዘ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ከአ/ማሕበሩ ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ እና አፍዴራ ከሚገኘው ፐላንት ጽ/ቤት በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ፡፡

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ም/ወረቀት፣ ለተእታ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ ከሚመለከተው የገቢዎች መ/ቤት በጨረታ ለመካፈል የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉና በመስኩ የተሰማሩ ባለሞያዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተጠቀሰው ዝርዝር ሥራ በተጨማሪ የሚጠገነውን ሕንጻ ቦታው ድረስ በመገኘት እና በማየት በነበረበት ሁኔታ ለመመለስ /በሰነዱ ላይ በተጠቀሰው ሁኔታ መልሶ ለመስራት/የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ አፍዴራ በማምረቻ ፋብሪካው ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የአስተዳደር ቢሮ እና በአዲስ አበባ በዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ቀን ታህሣሥ 4/4/2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጁ የጨረታ ሣጥኖች ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በአፋር ጨው ማምረቻ አ/ማሕበር ስም የተዘጋጀ የማንኛውም ህጋዊ የሀገር ውስጥ ባንክ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

ጨረታው በጨረታው መክፈቻው ሥ/ሥርዓት ለመገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታህሣሥ 4/4/2018 ዓ.ም. በ4:30 ሰዓት አፍዴራ የአ/ማሕበሩ የጨው ማምረቻ ሳይት አስተዳደር ጽ/ቤት እና በአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡

አክስዮን ማሕበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

አድራሻ ፡- አ/አ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 07 እከሱም ሆቴል አጠገብ በየነ ፀበሉ ሕንጻ 7ኛ ወለል

አፍዴራ አሊገንዳ ቀበሌ ጨው ማምረቻ

 

የአፋር ጨው ማምረቻ አ/ማኅበር

 

Save Tender