አፋር ጨው ማምረቻ አ/ማህበር አፍዴራ ለሚገኘው የጨው ማምረቻ ሳይት አጠቃላይ ስፋታቸው በግምት 40,000 /አርባ ሺ/ ስኳር ሜትር በሆኑ ክሪስታላይዜሽን ፖንዶች ውስጥ ተከማችቶ የሚገኘውን ግምቱ 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሣ ሺ) ኪዩቢክ ሜትር የጨው ምርት ቆፍሮ ከስክሶና ሰብስቦ፣ ለመጫን ዝግጁ የሚያደርግ ባክሆ ሎደር በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
የአፋር ጨው ማምረቻ አ/ማህበር
የባክሆ ሎደር ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 09/2017
አፋር ጨው ማምረቻ አ/ማህበር አፍዴራ ለሚገኘው የጨው ማምረቻ ሳይት አጠቃላይ ስፋታቸው በግምት 40,000 /አርባ ሺ/ ስኳር ሜትር በሆኑ ክሪስታላይዜሽን ፖንዶች ውስጥ ተከማችቶ የሚገኘውን ግምቱ 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሣ ሺ) ኪዩቢክ ሜትር የጨው ምርት ቆፍሮ ከስክሶና ሰብስቦ፣ ለመጫን ዝግጁ የሚያደርግ ባክሆ ሎደር በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቲ.ኦ.ቲ ከፋይ የሆነ፤ በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ የካቲት 18 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ዋናው መ/ቤት በሚገኘው ቢሮ ቁጥር 5 ወይም አፍደራ ከሚገኘው ገንዘብ ቤት በመቅረብና ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መጫረት የምትችል መሆኑን እየገለጽን
- የጨረታ ሰነዱን ከአፍዴራ የጨው ማምረቻ ሣይት የገዙ ተጫራቾች ጨረታ ሳጥኑ ባለበት በአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት በንግድ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በአፋር ጨው ማምረቻ አ/ማሕበር /Afar Salt Production SC/ ሥም ማስያዝ አለባቸው::
- ተጫራቾች በአንድ ካሬ ሜትር ስፋት ላይ የሚገኘውን ጨው ቆፍረው ከስክሰውና ሰብስበው ለመጫን ዝግጁ የሚያደርጉበትን ዋጋ ከጨረታ ሰነድ ጋር በተያያዘው ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው የካቲት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሆኖ በዕለቱ የካቲት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው በንግድ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- 22 አክሱም ሆቴል አጠገብ በየነ ጠበሉ ሕንጻ 7ተኛ ወስል
ስልክ ቁጥር ፡- 0116187073
አፋር ጨው ማምረቻ አ/ማህበር
