በላይነህ ክንዴ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ወደ ተለያዩ የግንባታ ፕሮጀክት ሳይቶች የኮንስትራክሽን ግብዓቶች (ጭነት) የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የትራንስፖርት አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል::
Belayneh Kindie Group (በላይነህ ክንዴ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ)
በድጋሚ የወጣ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
በላይነህ ክንዴ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ወደ ተለያዩ የግንባታ ፕሮጀክት ሳይቶች የኮንስትራክሽን ግብዓቶች (ጭነት) የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የትራንስፖርት አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል:: በመሆኑም ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና በቂ ተሽከርካሪዎችን ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ትራንስፖርተሮች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፦
- ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራጮች የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ግዥ ክፍል መውሰድ ይቻላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ ዋጋቸውን በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው::
- ጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋው 10 ፐርሰንት ሆኖ ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺ ብር) ያልበለጠ መሆን አለበት:: የጨረታ ማስከበሪያው በጥሬ ገንዘብ፣ በቼክ ወይም ባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ፣ ለብቻ በአነስተኛ ፖስታ በስም በታሸገ ዋጋ ማቅረቢያ ወይም ፕሮፎርማ ኢንቮይስ መቅረብ ይኖርበታል፤
- ከላይ ከተጠቀሱት ማስረጃዎች እና ሌሎችም ተወዳዳሪዎች ለውድድር ይጠቅመኛል የሚሏቸው ማስረጃዎች መቅረብ ይችላሉ::
ከላይ የተጠቀሱት ሁሉም ማስረጃዎች በትልቅ ፖስታ ውስጥ በስም ታሽገው እና ማህተም አርፎባቸው መቅረብ እና አራት ኪሎ፣ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ህንጻ የምድር ወለል በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ እስከ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን አስመዝግበው እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው::
የጨረታ ሳጥኑ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: አሸናፊዎች ጨረታውን ማሸነፋቸውን ድርጅቱ ከአሳወቀ ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለባቸው:: በተጠቀሰው ጊዜ ውል ካልያዙ የጨረታ ማስከበሪያው ገንዘብ ተመላሽ አይሆንም::ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
