Tender Detail

Tender Details

  • Company Tsehay Insurance S.C (TISC) (ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ)
  • Address ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 25111111970
  • Websitehttps://tsehayinsurance.com/
  • Deadline31 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazinereporter
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Security50,000.00 ብር (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም ያለ ቅድመ ሁኔታ በሚፈጸም የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee)
  • opening dateጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ
  • Categories Shipping and Logistics Services and Materials , Freight Transport

ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መሥሪያ ቤቱን በአሁኑ ቦታው (ቦሌ ድልድይ የቀድሞው ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት) ከሚገኘው ቢሮ አዲስ ወዳስገነባው ዋና መ/ቤት አድራሻ (አዲስ አበባ ሬስቶራንት ፊት ለፊት፣ ደጃዝማች ውቤ አካባቢ) ለማዛወር ይፈልጋል፡፡

Tsehay Insurance S.C (TISC) (ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ)


ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ.

ለ3ተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ፡

የቢሮ ዕቃ ማዛወር አገልግሎት ግዥ

ቁጥር፡- ፀኢ/ግንአ/006/2019

ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መሥሪያ ቤቱን በአሁኑ ቦታው (ቦሌ ድልድይ የቀድሞው ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት) ከሚገኘው ቢሮ አዲስ ወዳስገነባው ዋና መ/ቤት አድራሻ (አዲስ አበባ ሬስቶራንት ፊት ለፊት፣ ደጃዝማች ውቤ አካባቢ) ለማዛወር ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፣ ኩባንያው የቢሮ ዕቃዎችን (ጠረጴዛዎች፣ ወንበሮች፣ የኮምፒውተርና የሰርቨር ዕቃዎችን ወዘተ) እና የተለያዩ የኩባንያውን ሰነዶች በጥንቃቄ በማሸግ፣ በመጫን፣ በማጓጓዝ እና በማውረድ/በማደራጀት የተረጋገጠ ልምድ ያላቸውን ብቁ ድርጅቶች በዚህ ክፍት ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

ከተጫራቾች የሚጠየቁ መስፈርቶች፡

  1. ተጫራቾች ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ሊኖራቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ፋይናንሻል ተቋማትን ጨምሮ ለትልልቅ ድርጅቶች ተመሳሳይ ስራዎችን በመስራት የ5 ዓመት ልምድ እና አቅም እንዳላቸው እንዲሁም ስራውን ማከናወናቸውን የሚገልጽ ወቅታዊ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች አስፈላጊ የሆኑ የማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን እና የማሸጊያ ቁሳቁሶችን የማቅረብ አቅም ሊኖራቸው ይገባል፡፡
  4. ተጫራቾች ስራውን ለማጠናቀቅ የሚፈጅባቸውን ጊዜ የሚያሳይ የሥራ መርሃ ግብር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ፡ ተጫራቾች 50,000.00 ብር (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም ያለ ቅድመ ሁኔታ በሚፈጸም የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. አገልግሎት ሰጪው በእንቅስቃሴው ሂደት ለሚደርስ የሰነድ መጥፋት ወይም ጉዳት የኢንሹራንስ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

የጨረታ ሂደት፡-

  • የጨረታ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቦሌ ድልድይ የቀድሞ ብራስ ሆስፒታል ፊትለፊት በሚገኘው 3ኛ ፎቅ የኩባንያው የፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ፣ ከጥቅምት 18/2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ድረስ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • የጨረታ ማስረከቢያ፡ የተሟላ የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  • የጨረታ መክፈቻ፡ ጨረታው ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  • የኩባንያው መብት፡ ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • የቢሮ[…] ጉብኝት፡ ተጫራቾች የሁለቱንም ሕንፃዎች አቀማመጥ እ[…]ሚዛወሩ ዕቃዎችን አይነትና መጠን ለመገምገም የሚያስችል የቅድመ-ጨረታ የጉብኝት ፕሮግራም ጥቅምት 18-20/2019 በስራ ሰዓት ማየት ይቻላል፡፡

አድራሻ፡- ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መሥሪያ ቤት ቦሌ ድልድይ፣
የቀድሞው ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት

ስልክ፡ +251 111 119 70 / +251 116 50 66 30

✨ messages.ai_summary
Tsehay Insurance S.C invites qualified firms to move office furniture, computers, servers and documents from its current head office to a new one in Addis Ababa, including careful packing, loading, transport and unloading. Bidders need a valid trade licence, tax clearance, 5 years' similar experience and proof of vehicles and packing materials.
Save Tender