Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline16 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityግልጽ ጨረታ: ጠቅላላ ዋጋ 5% CPO ለእያንዳንዱ ኮድ፤ ሐራጅ: ኮድ01 300,000፣ ኮድ02 10,000፣ ኮድ03 40,000፣ ኮድ04 50,000፣ ኮድ05 4,000፣ ኮድ06 30,000፣ ኮድ07 25,000፣ ኮድ08 10,000፣ ኮድ09 2,000
  • opening dateተጫራቾቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደት በኦንላይን መከታተል ይችላሉ።
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተወረሱ የመገናኛ መሳሪያዎች፣ አልባሳትና ጫማዎች፣ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ መዋቢያዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች፣ የምግብ ነክ ዕቃዎች እና የመኪናና ሞተር ሳይክል መለዋወጫዎችን በጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 15/2019 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ።

በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ቅ/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር- 15/2019

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ

የሀዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት፣ የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጫርቃጨርቅ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች ፣የተለያዩ የምግብ ነክ ዕቃዎች፣ የመኪና እና የሞተር ሳይክል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ እና ሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች (ግለሰብም ሆነ ድርጅት) ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ጥራቱን በጠበቀ ስካን በማድረግ ኦንላይን የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው ጊዜ መሰረት በማንኛውም ጊዜና ሰዓት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ኦንላይን በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን C.P.O ለእያንዳንዱ ኮድ በማሠራት ያሠሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. ቅ/ጽ/ቤቱ ቢሮ ወይም ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በአካል በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
  4. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን የግልጽ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው ቀን ህዳር 02 ቀን 2019 ጀምሮ ህዳር 07 ቀን 2019 ጠዋት 4:00 ሰዓት ላይ ይዘጋል።
  5. የሐራጅ ጨረታው በተመሳሳይ ኅዳር 02 ቀን 2019 ተጀምሮ ኅዳር 07 ቀን 2019 ረፋድ 6:00 ሰዓት የሚዘጋ ሲሆን ተጫራቾቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደት በኦንላይን መከታተል ይችላሉ። በዚህ ጨረታ ላይ ለቀረቡት ዕቃዎች ተጫራቾች የሚሰጡት የሐራጅ ጨረታ የማሸነፊያ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ን ያካተተ ሲሆን ለኮድ 01 ብር 300,000፣ለኮድ 02 ብር 10,000፣ ለኮድ03 ብር 40,000፣ ለኮድ04 ብር 50,000፣ ለኮድ05 ብር 4,000፣ ለኮድ06 ብር 30,000፣ ለኮድ07 ብር 25,000 ለኮድ08 ብር 10,000 እና ለኮድ09 ብር 2,000 ለእያንዳንዱ ኮድ የዋስትና ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ በመመዝገብ የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
  7. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም ።
  8. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስኪያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
  9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት C.P.O በሶስት (3) ቀናት የሚመለስላቸው ይሆናል።
  10. ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ በተለጠፈው ፎቶ ብቻ ተመስርተው ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም።
  11. ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው።
  12. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል።
  13. ተጫራቾች የሚጭኑት/የሚያቀርቡት /ሰነድ ጥራቱን በጠበቀ መሳሪያ ስካን የተደረገ እና አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች ብቻ እንዲያቀርቡ ይመረጣል።
  14. ቅ/ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ:- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ በመመዝገብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ 09-05-11-55-11 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ:- የመንግሥት ጉምሩክ መጋዘን ሥራ ሂደት የስልክ ቁጥር:- 046-212-53-96 / 046-220-1936 ይደውሉ።

የቴሌግራም ግሩፕ:- https://t.me/hawassaawegaged (ECCH-ዕቃ አወጋገድ ሥራ ሂደት 2018)

በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Customs Commission Hawassa Branch sells confiscated goods as is, by online open tender and auction via Auction Ethiopia: communication devices, clothing and textiles, electrical items, cosmetics, home and office items, food items, and vehicle and motorcycle parts.
Save Tender