በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት በዞን አስተዳደር ስር በሚገኙ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች የሚሆን ጽህፈት መሣሪያና የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በንጥል ዋጋ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት በዞን አስተዳደር ስር በሚገኙ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች የሚሆን ጽህፈት መሣሪያና የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በንጥል ዋጋ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች በዝርዝር የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ፤
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለው፤
- ተጫራቾች የ2018 የአንድ አመት ታክስ ክሊራንስ /TAX CLEARANCE/ማቅረብ የሚችል
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቀረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ 100,000 /አንድ መቶ ሺህ / ብር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ፤
- የሚጠየቁ ናሙና አይነቶችን ማቅረብ የሚችል፤ ናሙናዎችን ዞን ፋይናንስ ማየት ይችላሉ/፤
- ተጫራቾች ከላይ ከ1-7 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸውጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በመንግስት የሥራ ሰዓት ማስገባት ይቻላል፤
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 ብር በመክፈል ከጎፋ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ያገኛሉ።
- የጨረታ አሸናፊው ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ እስከ ሳውላ ከተማ ጎፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ንብረት ክፍል አምጥቶ በተያዘው ናሙና መሠረት ማስረከብ አለበት።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ መኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ በ16ኛው ቀን ጠዋት3:00 ታሽጎ በዕለቱ በ16ኛው ቀን ለጠዋቱ 3:30 ጨረታው ይከፈታል። 16ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና ዕሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የመንግስት የሥራ ቀን ይከፈታል ።
ማሳሰቢያ፤-
* መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
* ለተጨማሪ ማብራሪያ - የስ.ቁ 09-16-48-07-37 ይደውሉ!!
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
✨ messages.ai_summary
Gofa Zone Finance and Plan Development Department, South Ethiopia, buys stationery and cleaning items for zone departments and offices by open tender, compared by unit price. Bidders need a renewed sector licence, trade registration, VAT, TIN, 2018 tax clearance and supplier registration.
