Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline20 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ CPO ለእያንዳንዱ ሎት ብር 30,000 በሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስም በማሰራት
  • opening date4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች / ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት/ባልተገኙበት ይከፈታል።
  • Categories Carpets And Curtains , Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials

የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ ለቢሮ ለስራ አገልግሎት የሚዉሉ እቃዎችን ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ ለቢሮ ለስራ አገልግሎት የሚዉሉ እቃዎችን ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት.1 ስቴሽነር ዕቃዎች
  • ሎት.2 የጽዳት ዕቃዎች
  • ሎት.3 መጋረጃ እና መሰል ዕቃዎች

በዚሁ መሠረት፤- ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ሊያሟላ የሚችል ተወዳዳሪ መወዳደር ይችላል።

  1. የመስኩ የታደሠ ንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  3. የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ወረቀት(ታክስ ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችል፤
  4. ቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
  5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
  6. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1- 6 የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት 500( አምስት መቶ ብር) በባንክ አካዉንት በመክፈል በሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ሠነዱን መውሰድ ይቻላል ።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ CPO ለእያንዳንዱ ሎት ብር 30,000 በሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. ተጫራቾች የፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጂናል1 እና 2 ኮፒ በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል ።
  11. ጨረታው ጋዜጣ ከወጣበት ከ10 ተከታታይ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች / ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት/ባልተገኙበት ይከፈታል ። ዕለቱ በዓል ከሆነ / የስራ ቀን ካልሆነ/ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለጸው ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።
  12. መ/ቤቱ ለናሙና የሚፈልጋቸውን ዕቃ ከጨረታው ሰነድ ጋር የሚገለጽ ሲሆን ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለተጠየቀ ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው ።
  13. የጨረታ አሸናፊ ዕቃውን በራሱ ወጪ አጓጉዞ መጋዘን ማስገባት ይኖርበታል።
  14. የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ መሠረት የጨረታ አሸናፊነቱ በዉስጥ ማስታወቂያ ይገለጻል።
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0916809029

የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Hawassa City First Instance Court buys office supplies in three lots by open tender: stationery, cleaning items, and curtains and similar items. Bidders need a renewed trade licence, trade registration, tax clearance, VAT, TIN and supplier registration.
Save Tender