ስኬት ባንክ አ.ማ የጽህፈት እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል::
Siket Bank S.C (ስኬት ባንክ አ.ማ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር SB/OT/NCB/12/04/2026
ስኬት ባንክ አ.ማ የጽህፈት እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል:: ስለሆነም :- ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው:-
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
- ወቅታዊ የሆነ የታክስ ክሊራንስ በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጣቸውን ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር /Suppliers List/ ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በማናቸውም የስራ ሰዓት / ከሰኞ እስከ ቅዳሜ / ከባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 410 የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 600 /ስድስት መቶ ብር /በመክፈል ሰነድ ገዝታችሁ በ16ኛው የስራ ቀን በባንኩ ዋ/መቤት ቢሮ ቁጥር 407 ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 5:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸኋል:: ጨረታው በዚሁ እለት በ5:00 ሰዓት ተዘግቶ በ5:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ባይገኙም የጨረታ ኮሚቴው እና ጨረታው የተሟላ ከሆነ የቴክኒካል ሰነድ ብቻ የሚከፈት ሲሆን የፋይናንሻል ሰነድ የሚከፈተው የሳምፕል ውጤታቸው ብቁ የሆነ ብቻ ይሆናል::
- ተጫራቾች አንድ ቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ አንድ ቴክኒካል ኮፒ ሰነድ እና አንድ ኦርጅናል ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኮፒ ፋይናንሻል ሰነድ በፖስታ ለየብቻው በማሸግ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው::
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊ ተጫራቾች ከውድድሩ በራሳቸው ፈቃድ ቢወጡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለባንኩ ገቢ ይሆናል::
- ለዕቃዎቹ ሞልተው የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ማካተት ይኖርበታል::
- ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በሚመልሱበት ጊዜ በሰነዱ ላይ በተጠቀሰው ልክ ናሙና /Sample/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውድቅ ይደረጋል::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዝርዝር ዋጋ በሚመለከት ከባንኩ በወሰዱት ሰነድ ላይ የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት ቅጽ መሰረት ሞልተው መመለስ ይኖርባቸዋል::
- ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ፣ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ፣ ያልታሸገ ሰነድ፣ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ ያልተደረገበት ሰነድ ከጨረታ ውድድር ያሰርዛል::
- አሸናፊው ከተለየ በኋላ ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወይም ቢድ ቦንድ ይመለስላቸዋል::
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቹ የጨረታ ሰነዱን በሚመልሱበት ጊዜ ተጫራቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሉ የጨረታ ሰነዱን ሞልቶ ስለመላኩ የሚገልፅ ቅፅ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ሞልተው በፊርማና ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታው መክፈቻው ቀን በስራ ቀን ካልዋለ የጨረታው መዝጊያውም ሆነ የመክፈቻው ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በሚውልበት ቀን እና ሰዓት መሰረት ከላይ በተገለጸው የመዝጊያና የመክፈቻ ስነ- ስርዓት ሰዓት መሰረት የሚከናወን ይሆናል::
| ተ.ቁ | የሚገዛው የዕቃ ዓይነት | Cpo or unconditional bank guarantee |
| 1 | የጽህፈት እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ | 250,000 |
የባንኩ የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ 2:00 -11:00 ብቻ ነው::
አድራሻ:- ፒያሳ ቸርችል ጎዳና ከቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ሃሮን ታወር ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር: 011 1 27 55 85
ስኬት ባንክ አ.ማ
✨ messages.ai_summary
Siket Bank S.C. seeks suppliers of stationery and cleaning materials. Bidders must submit samples as specified in the tender document; financial offers are opened only for those whose samples qualify. Open bid.
