Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ኮሚሽን
  • Address , Phone: ..........
  • Website
  • Deadline27 Nov 2026, 10:15 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 200.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 5,000.00 (የባንክ ዋስትና ወይም CPO)
  • opening dateበዕለቱ ከሰዓት ከቀኑ 8:15
  • Sector Furniture And Furnishing , Cleaning And Janitorial Equipment , Electronics Materials

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ኮሚሽን የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችና ፈርኒቸር ግዥ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ኮሚሽን


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት በ "UNFPA and KOICA" ፕሮጀክት የወጣቶች ስብዕና ልማት ፕሮግራም በ1ኛ እና 2ኛ መንፈቅ ዓመት የወጣቶች ስብዕና ማዕከላት ቁሳቁስ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤ በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱ ሎቶችን ማለትም:- ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ አላቂ ዕቃዎች ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እና ፈርኒቸር ግዥን ከዚህ በታች የተጠቀሱ ቴክኒካል መስፈርቶችን ከሚያሟሉ ለግዴታዎች ተገዢ ከሚሆኑ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል::

  • የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
  • የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  • የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ማቅብ የሚችሉ፣
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
  • የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  • በግዥ ፈፃሚ መ/ቤቱ የሚዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ ከፍሎ መግዛት የሚችል፤
  • ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው ከረፋዱ 4:15 ገብቶ በዕለቱ ከሰዓት ከቀኑ 8:15 እጩ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይሆናል ባይገኙም የጨረታው ሂደት አይስተጓጎልም፤
  • ህጋዊነቱ ከተረጋገጠ ፋይናንሻል ተቋም/ባንክ/ 5,000.00/አምስት ሺህ ብር ብቻ/ ዋጋ ያለውን የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ሲፒኦ ማቅረብ የሚችልና ለዉል አስተዳደር መመሪያ መሠረት ተገዢ የሚሆን፤
  • ተጫራቾች የጨረታ ዋጋቸዉን ከግዥ ፈፃሚው መ/ቤት በሚገዙት የጨረታ ሠነድ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በሁለት ኮፒ በሰም በታሸገ ፖስታ ስማቸዉንና አድራሻቸውን በመሙላትና በሁሉም ዋጋ መሙያ ሠነዶች ላይ ፊርማ ናሙናቸውን በማሳረፍ በአንድ እናት ፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸኋል፤
  • አሸናፊዉ ድርጅት ያሸነፋቸውን የዕቃዎች ጥራት፣ ዓይነት፣ ለአቅርቦት ጊዜ ገደብና ብዛት ማረጋገጫ ውል መግባት ይኖርባቸዋል፤
  • መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ የግዥውን መጠን እስከ 20% የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  • ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር +251916158789፣ +251900119718፣ +251912466781 እና +251916853492 ደውሎ ማግኘት ይችላሉ::

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ኮሚሽን

Summary
South Ethiopia Region Youth Affairs and Volunteer Service Commission seeks suppliers of electronics, consumable hygiene/cleaning items and furniture for youth personality development centres under the UNFPA and KOICA project. Open bid.
Save Tender