Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ማቴሪያሎቹን በሀገራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


የ2ኛ ዙር ሀገራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ማቴሪያሎቹን በሀገራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት የሕንፃ መሣሪያ ግዥ
  • ሎት የጽሕፈት መሣሪያ ግዥ
  • ሎት የቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ
  • ሎት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ
  • ሎት የሞተርና መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ
  • ሎት የጄኔሬተር ግዥ

ሎት7:-አሸዋ በቢያጆ ጠጠር 02 በማሽን የተፈጨ በቢያጆ የፍልጥ ድንጋይ በቢያጆ፣ የሞሉት ድንጋይ በቢያጆ ቡሎኬት ባለ-10 ቡሎኬት ባለ-15 ቡሎኬት ባለ-20

ሎት8:-የሴክተር መ/ቤቶች መኪናዎች ጥገና ጉልበት ዋጋ እና መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ - አምቡላንስ መኪና ታርጋ-04266 የላንድ ኩሩዘር መኪና ታርጋ-30793 የቀይ መስቀል መኪና ታርጋ-02337 እና ፓትሮል መኪና ታርጋ-0401 ጥገና ማድረግ፤

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ ተሻሽሎ በወጣው በመንግሥት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 70/2017 ዓ.ም መሰረት:-

  1. የ2019 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉበት መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
  3. የግብር ከፋይነት ምዝገባ ቁጥር /Tin Number/ ያላቸው፤
  4. የቫት ተመዝጋቢ የሆነበት መረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፤
  5. ከሽያጭ ዋጋ ላይ ለመንግሥት ግብር 3% ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ፤
  6. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  7. የዕቃ አቅራቢነት በኦንላይን የተመዘገበበትን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  8. የጨረታ ሁኔታ በአይቴም ወይም በጥቅልል ሊሆን ይችላል፤
  9. የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በመለየት ኦርጂናሉንና ኮፒውን የጨረታ ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማስገባት በሰም በታሸገው ኤንቨሎፕ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በቁጫ አልፋ ወረዳ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ-5 ላይ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፤
  10. በጨረታ ሂደት ላይ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የውል ማስከበሪያ 25% ማስያዝ ግዴታ አለባቸው።
  11. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል ።
  12. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ የማይመለስ 400/አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ወደ ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር-5 ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት የሚችሉ ይሆናል።
  13. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ ሕጋዊ Cpo/እና በጥሬ ገንዘብ ከሚገዙበት 25,000/ ሃያ አምስት ሺህ ብር ብቻ የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፤
  14. የጨረታ ሣጥን የሚታሸገው የጨረታ ማብቂያ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10:00 ሰዓት ይሆናል፤
  15. ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤
  16. በጨረታው አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ዕቃውን እስከ ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ድረስ የጫኚ አውራጅ እና የጭነት ወጪን በመሸፈን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  17. ተጫራቾች ወይም የጨረታ ወኪል ያለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አስተጓጉልም፤
  18. የ16ኛው ቀን ሰንበት ወይም በዓል ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፤

ማሳሰቢያ:-

  • በጨረታው አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ የዕቃው ከጥራትና ደረጃ ዝቅ ቢል፣ ዕቃው ቢጓደል ከተዋዋ ለው ከውሉ ጊዜው ቢያልፍ በሕግ መሰረት ለመንግሥት ከገባሁት ከጠቅላላ ውል ገንዘብ ላይ 25% ያሀሉን የሚደርሰውን ብር ተቀጥቶ ገንዘብ ተመላሽ ለማድረግ በፍ/ህ/ቁጥር 3132 መሰረት የፀና ይሆናል።
  • ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት በሕግ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ 0980140919 /0976135648/0984666189 ደውለው ይጠይቁ።

በቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Kucha Alfa Woreda Finance and Plan Development Office, Gamo Zone, South Ethiopia, buys in a second-round open tender: building materials, stationery, office furniture, electronics, motor parts, a generator, sand, gravel and blocks, and repair of four office vehicles.
Save Tender