ሲዳማ ኤልቶ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ከሃዋሳ ማእከል የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዝ አገልግሎት
ሲዳማ ኤልቶ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ኃ.የተ
የጨረታ ማስታወቂያ
ሲዳማ ኤልቶ የገበሬዎች ኅ/ስራ ዩኒየን በያዝነው 2019/20 ምርት ዘመን ከሃዋሳ ማእከል የበልግና መኸር የአፈር ማዳበሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል ። ስለሆነም ተጫራቾች ከድርጅቱ የማራገፊያ ጣቢያዎች ዝርዝር መግለጫ ሰነድ በመውሰድ ለማጓጓዝ የሚፈልገውን የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፋልት መንገድ በአማካይ በኩንታል በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል። በዚሁ መሰረት ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር ከፍሎ ፈቃዱን ያሳደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው።
- ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የስራ ዘርፍ ተሰማርቶ በአንድ ጊዜ ኮንትራት ውል 50000 ኩንታል በላይ በማጓጓዝ ስራውን በሚገባ ስለመወጣቱ የመልካም ስራ አፈፃፀም ቢያንስ ሶስት ማቅረብ የሚችል።
- የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር ያመች ዘንድ በአንድ አከባቢ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችሉም።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 200,000.00 / ሁለት መቶ ሺህ ብር / ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታ አሸናፊ የሚሆን ማንኛውም ድርጅት ውል ከመፈፀሙ በፊት ያሸነፉበትን ጭነት የማጓጓዣ ዋጋ 10 % በቅድሚያ ያስይዛል።
- ተጫራቾች የተሽከርካሪዎች ዝርዝር ቢያንስ 2000/ሁለት ሺህ/ ኩንታል በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችሉ መኪናዎችን /የሰሌዳ ቁጥር የሻንሲ ቁጥር ፣የመኪና ዓይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠው መንግስታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ለሚጠፋው ንብረት በሙሉ ሃላፊነት የሚወስድ የጭነት ኢንሹራንስ /ካርጎ ኢንሹራንስ/ ያለውና መረጃውን ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከሲዳማ ኤልቶ የገበሬዎች ኅብረት ስራ ዩኒየን ዋና ፅ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውል ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካል ዶክመንት 1 ኦሪጅናልና 1 ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ዶክመንት ኦሪጅናል 1 እና ኮፒ 1 ለየብቻው ሆኖ በአንድ እናት ካኪ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ10ኛው የስራ ቀን የጨረታ ሰነዳቸውን በመሙላት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ ቀኑ 9:30 የሚያስገቡና ከቀኑ 10:00 ታሽጎ በ10:30 የጨረታው ሳጥን ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በዩኒየኑ ዋና ፅ/ቤት ይከፈታል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ፡- ፅ/ቤት ድረስ በአካል በመቅረብ አልያም በስ.ቁ 046-212-4704 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
ሲዳማ ኤልቶ ኃ.የተወሰነ ኅ/ሥራ ዩኒየን
✨ messages.ai_summary
Sidama Elto Farmers Cooperative Union seeks licensed transporters to haul fertilizer from its Hawassa center to its unloading stations, pricing per quintal for gravel and asphalt roads. Cargo insurance required. Open bid.
