Tender Detail

Tender Details

  • Company መሊቅ የስልጤ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ
  • Address , Phone: 0936488818
  • Website
  • Deadline25 Nov 2026, 2:45 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000(አንድ ሺህ ብር)
  • Bid Securityተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 300,000(ሶስት መቶ ሺህ ብር) በመሊቅ የስልጤ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ስም በማሠራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
  • opening dateበ16ኛው ቀን ወይም በዚያው ቀን 09:00 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒየኑ ጽ/ቤት ይከፈታል፣
  • Categories Freight Transport

መሊቅ የስልጤ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንግሥት በስልጤ ዞን ለሚገኙ ወረዳዎች ላሉ አርሶ አደሮች በያዝነው 2019 ዓ.ም በወራቤ ከተማ ከሚገኘው ማዕከላዊ መጋዘን ለሰብል አብታይ ወረዳ፣ጣቢያዎች በበልግና በመኸር የአፈር ማዳበሪያ ምጥንና ዩሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፣

መሊቅ የስልጤ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ


ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 003/2019

መሊቅ የስልጤ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንግሥት በስልጤ ዞን ለሚገኙ ወረዳዎች ላሉ አርሶ አደሮች በያዝነው 2019 ዓ.ም በወራቤ ከተማ ከሚገኘው ማዕከላዊ መጋዘን ለሰብል አብታይ ወረዳ፣ጣቢያዎች በበልግና በመኸር የአፈር ማዳበሪያ ምጥንና ዩሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፣ ስለሆነም ተጫራቾች ከዩኒየኑ የማራገፊያ ጣቢያዎችን ዝርዝር መግለጫ በመውሰድ ለማጓጓዝ የሚፈልጉትን የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፓልት መንገድ በአማካኝ በኩንታል፣ በአንድ ኪሎ ሜትር ተሰልቶ በእያንዳንዱ ጣቢያ በማሳየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፣

በዚህም መሰረት:-

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ የንግድ ፍቃድ ያሳደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅቶች ከሆኑ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፣
  2. ከሚመለከተው ፍቃድ ሰጪ መንግሥታዊ አካል የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
  3. ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ስራ ዘርፍ ተሰማርቶ ሥራውን በሚገባ ስለመወጣቱ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችል፣
  4. የጨረታ ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በዞኑ ውስጥ ባሉ ወረዳ ማራገፊያ ጣቢያዎች በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችሉም፣
  5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 300,000(ሶስት መቶ ሺህ ብር) በመሊቅ የስልጤ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ስም በማሠራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
  6. በጨረታ አሸናፊ የሚሆነው ማንኛውም ድርጅት ውል ከመፈፀሙ በፊት ያሸነፈበትን ጭነት የማጓጓዣ ዋጋ 5% በቅድሚያ ሕጋዊ በሆነ ዋስትና ያስይዛል/ያሠራል፣
  7. ተጫራቾች የተሽከርካሪዎች ዝርዝር ቢያንስ 2000(ሁለት ሺህ) ኩንታል በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችሉ መኪናዎችን የሰሌዳ ቁጥር፣ የመኪና ዓይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ፍቃድ ከሰጠው መንግስታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አይይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  8. የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ) ብር በመክፈል ከዩኒየኑ ዋና ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛትና መውሰድ ይችላል፣
  9. የጨረታው ሰነድ በኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላል፣
  10. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8:45 ታሽጎ በ16ኛው ቀን ወይም በዚያው ቀን 09:00 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒየኑ ጽ/ቤት ይከፈታል፣ ነገር ግን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሁኔታ መሰረት ይከፈታል፣
  11. ተጫራቾች አዲሱን የገንዘብ መቀበያ /QR COD/ ሊኖራቸው ይገባል፣
  12. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረት መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ:- ስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ከወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር ሞባይል:- /0949-26-13-35/ /0936-48-88-18

መሊቅ የስልጤ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ

✨ messages.ai_summary
Melik Silte Farmers Cooperative Union seeks transporters to deliver blended fertiliser and urea from its Worabe central warehouse to woreda stations across Silte Zone, Central Ethiopia, by open tender. Bidders need trucks able to carry at least 2,000 quintals at once.
Save Tender