በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አቤቤ ቱፋ ቅድመ አንደኛ እና አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለመሥራት ይፈልጋል።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚኩራ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት አቤቤ ቱፋ ቅ/አ/አ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አቤቤ ቱፋ ቅድመ አንደኛ እና አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለመሥራት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚመለከታቸው ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ሎት1:- የደንብ ልብስ
- ሎት2:- መጻሕፍት እና ልዩ ልዩ መሣሪያዎች
- ሎት3:- የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት 4:- የሕትመት ሥራዎች
- ሎት5:- የሕክምና ዕቃዎች
- ሎት 6:- አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
- ሎት7:- ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት8:- ቋሚ የቢሮ እቃዎች (የፈርኒቸር ውጤት)
- ሎት9:- የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት10:- የትራንስፖርት አገልግሎት
- ሎት11:- የኤሌክትሮኒክስ ጥገና
- ሎት12:- የተገጣጣሚዎች ጥገና እና እድሳት
- ሎት13:- አላቂ የቢሮ እቃዎች
በጨረታ መሳተፍ ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባችሁ:-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃቸውንና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀትና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ሕጋዊ ደረሰኝ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና
- ሎት1:- የደንብ ልብስ 40,000/ አርባ ሺህ ብር)
- ሎት2:-መጻሕፍት እና ልዩ ልዩ መሣሪያዎች 5,000 (አምስት ሺህ ብር)
- ሎት3:-የፅዳት ዕቃዎች 20,000 (ሀያ ሺህ ብር)
- ሎት 4:-ህትመት ሥራዎች10,000 (አስር ሺህ ብር)
- ሎት5:-የሕክምና ዕቃዎች 5,000 (አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 6:-አላቂ የትምህርት ዕቃዎች 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር)
- ሎት7:-ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እና ዕቃዎች 40,000/ አርባ ሺህ ብር)
- ሎት8:-ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር)
- ሎት9:-የደንብ ልብስ ስፌት10,000 (አስር ሺህ ብር)
- ሎት10:-ትራንስፖርት አገልግሎት 5000 (አምስት ሺህ ብር)
- ሎት11:-የኤሌክትሮኒክ እና ማሽነሪ ጥገና 10,000 (አስር ሺህ ብር)
- ሎት 12:-የተገጣጣሚዎች ጥገና እና እድሳት10,000 ( አስር ሺህ ብር)
- ሎት13:-አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 10,000 (አስር ሺህ ብር)
- ይህ ማስታወቂያ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ አስራ አንድ /11:00/ ድረስ ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አቤቤ ቱፋ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 01 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ ዕቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር በመግለጽ ፖስታ ሰነዱን በኦሪጂናልና ኮፒ በድርጅቱ ክብ ማህተም በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ ሣጥኑ ይታሸጋል፤ ስለዚህ ሁሉም ተጫራቾች ሰነዳቸውን አስገብተው ማጠናቀቅ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃዎች ዋጋ ሰነድ ሲያቀርቡ ኦሪጂናልና ደረጃውን የጠበቀ ናሙና በት/ቤቱ ግዥ ቢሮ ማድረግ አለባቸው።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች ተወዳድረው ካሸነፉበት ናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ጭነው የማቅረብና ደረጃውን ያልጠበቀ ዕቃ ከሆነ መልሰው ትክክለኛውን የማምጣት ግዴታ አለባቸው።
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ት/ቤቱ ውስጥ ሲሆን ጨረታው ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በአል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% /C.P.O/ በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በማንኛውም ግልጽ ጨረታ ላይ ቢልታገዱ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር መሆን አለበት።
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አቅራቢዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሆነ የዋስትና ደብዳቤ ካደራጃቸው አካል በጽ/ቤት ኃላፊ በኩል ተፈርሞ የቀረበ ዋስትና መሆን አለበት።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር አቤቤ ቱፋ ት/ቤት ልዩ ስሙ ቦሌ አራብሳ ሰፈራ አደባባይ ገባ ብሎ ቤ/ክ ሀይስኩል አጠገብ።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚኩራ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት አቤቤ ቱፋ ቅ/አ/አ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Abebe Tufa Primary and Middle School, Lemi Kura Sub-City Woreda 06, Addis Ababa, buys in 13 lots: uniforms and sewing, books, cleaning, printing, medical, school and office supplies, electronics, furniture, transport service and repairs. Licence, TIN, VAT and supplier list needed.
