የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቶዮታ አውቶሞቢል ተሽከርካሪ ግልጽ የጨረታ ሽያጭ
Modjo Customs Branch Office (የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
የመጀመሪያ ግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
ታክስ ከፋዩ አስመጪ INTEMA TRADING PLC የሚፈለግባቸውን ቀሪጥና ታክስ ብር 1,313,886.16 (አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ አስራ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ሰማንያ ስድስት ብር 16/100) ስላልከፈሉ አድራሻው አዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ 01 ቀበሌ የሆነውን የታክስ ባለእዳውን ሀብት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 41 ንዑስ አንቀጽ 9 እና በመመሪያ ቁጥር 208/2013 በተደነገገው መሰረት TOYOTA COHOLA CHASSIS NUMBER JTDBW23EX63105212, MANUFACTURED YEAR 2007, CYLINDER CAPACTY 1299CG አውቶሞቢል ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል::
- የሀብቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ግምት ብር 15,253,220.62 ነው::
- ስለሀብቱ አሻሻጥ መረጃ ከዕቃ አወጋገድ ቡድን ቢሮ ቁጥር 238 ስልክ ቁጥር 022-236-90-94 ደውለው ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች በቅድሚያ የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/10ኛውን በአክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን ፕላትፎርም ማስያዝ አለባቸው:: ተጫራቾች የወረቀት ሲ.ፒ.ኦ የሚያስይዙ ከሆነ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMSSON MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፣ አዳማና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት::
- ተጫራቾች ሀብቱን/ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጥቅምት 28/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ስለሚቆይ ዋጋ ማስገባት ይችላሉ::
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበትን ቀን ጨምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው ቀን ህዳር 15/2019 ዓ.ም ጠዋት 3:00 ሰዓት ስለሚዘጋ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታውን በአክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን ፕላትፎርም መከታተል ይችላሉ::
- አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከገዛው ዋጋ ጋር ታስቦ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ በመክፈል ሀብቱን መረከብ አለበት::
- የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ የማይከፍል ከሆነ ለጨረታው በዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ የጨረታው አሸናፊነቱ ይሰረዛል::
- ኮሚሽኑ ስለሀብቶቹ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል ሊሰርዝ ይችላል::
- ማንኛውም እድሜው 18 አመት እና በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የታደሰ መታወቂያ በማቅረብ ቅድመ-ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል::
የሞጆ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Modjo Customs Branch Office is selling a Toyota passenger car seized from a tax debtor, through the Auction Ethiopia online platform. Bidders deposit a tenth of the starting price. Open to Ethiopians aged 18 and over with valid ID. Online auction.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
