Tender Detail

Tender Details

  • Company የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን አንደኛ መካከለኛ እና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
  • Address መርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112759328
  • Website
  • Deadline18 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityተጫራቾች በእያንዳንዱ ምድብ ስር ለሚገኙት የሚጫረቱበትን እቃ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  • opening dateበዛው ዕለት በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቢሮ ቁጥር 219 መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
  • Categories Textile, Garment & Leather , Cleaning And Janitorial Equipment , Office And Home Furniture , Computer Laptop And Accessories , Laboratory Equipment And Chemicals , Stationery Materials , Sport Materials And Sportswear

የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን አንደኛ፣ መካከለኛ እና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃ፣ ኮምፒውተርና ላፕቶፕ፣ የቢሮ ቋሚ እቃ፣ የላብራቶሪ እቃ፣ የስፖርት እቃ፣ የደንብ ልብስና የጥገና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ያወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን አንደኛ መካከለኛ እና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን አንደኛ፣ መካከለኛ እና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተለያዩ የስራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ኮምፒውተሮችና ላፕቶፖችን ሎት 4 የቢሮ ቋሚ እቃዎችን ሎት 5 የላብራቶሪ እቃዎችን፣ ሎት 6 የስፖርት እቃዎችን፣ ሎት 7 የደንብ ልብሶችን፣ ሎት 8 የጥገና ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች

  1. ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቢሮ ቁጥር 212 በመምጣት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ::
  2. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ወይም አገልግሎት የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ክሊራንስ የሚያቀርቡ፣ መሆን መቻል አለባቸው::
  3. በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚገልፀው ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በታሸገ ኤንቨሎፕ በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቢሮ ቁጥር 212 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
  4. የዕቃው ጠቅላላ ዋጋ መቅረብ ይኖርበታል::
  5. ትክክለኛ አድራሻቸውን በማሸጊያ ኢንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ መፈረም አለባቸው::
  6. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ምድብ ስር ለሚገኙት የሚጫረቱበትን እቃ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል:: የሚያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል::
  7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቢሮ ቁጥር 219 መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል:: ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም::
  8. ተጫራቾች የጨረታው ውጤት ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከወጣ ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጽሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ10 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ በሙሉ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ሆኖም በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ማስገባት ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለትምህርት ቤቱ ገቢ ይደረጋል::
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃዎች ውል በመዋዋል የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ አጠቃለው ዕቃዎቹን በ10 ቀናት ውስጥ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፤አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በወቅቱ ገቢ ካላደረጉ የዕቃዎቹን ጠቅላላ ዋጋ 0.1% በየቀኑ የመቀጮት ይሰላባቸዋል::
  11. የንግድ ድርጅቶች ለጨረታ የሚሰጡት ዋጋ ከማንኛውም ግብር (Taxes) ጨምሮ መሆን አለበት::
  12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ላይ በየገፁ ስምና ፊርማ ማስገባት አለበት::
  13. ትምህርት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  14. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው::
  15. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ሲመልሱ የቴክኒካል ሰነዶቻቸውን እና የፋይናንስ ሰነዶቻቸውን ለየብቻ ከአንድ (1) ኮፒ ጋር በማያያዝ ማስገባት አለባቸው:: ሲፒኦ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ተያይዞ መግባት አለበት::
  16. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ለ90 (ዘጠና) ቀናት የፀና ይሆናል::
  17. የጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ አቅራቢዎች ከሚመለከተው አካል በትምህርት ቤቱ ስም የተጻፈ ደብዳቤ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  18. ለበለጠ መረጃ:- ስልክ ቁጥር +251-112-75 93 28/+251-112-76 54 24 የመ.ሣ.ቁጥር:-23351

አድራሻ:- መርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት

ማሳሰቢያ:-ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች ማሟላት ይገባቸዋል ይህ ካልሆነ ግን የጨረታ ሰነዳቸው ከጨረታ ውጪ እንደሆነ እንገልፃለን::

የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን አንደኛ መካከለኛ እና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

✨ messages.ai_summary
Debre Hayil St. Raguel Church School, Merkato, Addis Ababa, buys in 8 lots by open tender: stationery, cleaning items, computers and laptops, fixed office items, lab items, sports items, uniforms and maintenance items. Bidders need a renewed trade licence, VAT and tax clearance.
Save Tender