የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የመኪና ጎማ እና የእንስሳት መድሀኒት ግዥ
በማ/ኢ/ክ/መ/ ምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2019
በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች እና መዘጋጃ ቤቶች አገልግሎት የሚውል፤ ሎት1 የጽህፈት መሳሪያዎች፤ ሎት2 የተሽከርካሪ መኪና ጎማ፤ ሎት3 የእንስሳት መድሀኒት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል::
- የዘመኑ ግብር የከፈለ እና ስለመከፈሉ ከገቢዎች ጽ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል::
- ቲን ነምበር ያለው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ::
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው::
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው::
- ጨረታው የሚቆየው ከ28/2/2019 ዓ.ም እስከ 8/3/2019 ዓ.ም ሲሆን ተጫራቾች ዋጋቸውን በሁለት ፖስታ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ለየብቻ ቫትን አካተው በመሙላት ሶ/ወ/ፋይናንስ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁ/ር 8 በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ8/3/2019 ዓ.ም ሎት1 ከቀኑ 8:00 ሰዓት ታሽጎ በ8:30 ይከፈታል፤ ሎት2 በ8:30 ታሽጎ በ9:00 ሰዓት ይከፈታል፤ ሎት3 በ9:00 ታሽጎ በ9:30 ሰዓት ሶ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት የግ/ክ/ን/አስ/ሥ/ሂደት በግዢ ኬዝቲም ቢሮ ቁ/ር 8 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል::
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ከሎት1-ሎት3 ለእያንዳንዳቸው ብር 20,000/ሀያ ሺህ/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል::
- የጨረታ ማስከበሪያው ለተሸናፊ ድርጅት አሸናፊው ውል መግባቱ ከተረጋገጠ በኋላ ይመለስለታል::
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱን ከተረጋገጠ እስከ ሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመቅረብ ውል መፈጸም ይኖርበታል::
- አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች በፈረሙት ውል መሰረት አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች/አገልግሎቶች/ በራሳቸው ትራንስፖርት ፋይናንስ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የእቃው ዝርዝር የያዘ ሰነድ ሶዶ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ ከሎት1-3 ለእያንዳንዱ ብር 200/ሁለት መቶ/ በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይችላሉ::
ለበለጠ መረጃ:-0468830533/128/0576/
በማ/ኢ/ክ/መ/ ምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Sodo Woreda Finance Office (East Gurage Zone, Central Ethiopia) seeks suppliers in 3 lots: stationery, vehicle tyres and veterinary medicines for woreda sector offices and municipalities. Open bid.
