አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)
የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር አማራ ባንክ/57/2019
አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | የንብረቱ አድራሻ | የቦታው ስፋት | የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር | የንብረቱ ዓይነት/ የይዞታው አገልግሎት | የጨረታ መነሻ ዋጋ /ብር/ | ጨረታው የሚከናወንበት | |||||
| ከተማ | ክ/ከተማ | ወረዳ | ቀበሌ | ቀን | ሰዓት | ቦታ | ||||||||
| 1 | አቶ ሀብታሙ ሙጬ ተገኘ | አቶ ሙጬ ተገኘ የኋላ | ባህር ዳር | ባህር ዳር | ጣና | - | 16 | 249 ካ.ሜ | 302/2004 | ለመኖሪያ | 6,481,568.33 | ህዳር 25 ቀን 2019 ዓ.ም | ከ 4:00 እስከ 5:00 ሰዓት | አማራ ባንክ አ.ማ ባ/ዳር ዲስትሪክት ቢሮ (ባ/ዳር) |
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይም ሃያ አምስት በመቶ (25%) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) ብቻ በአማራ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት፣ በማስያዝ እና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ::
- ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው::
- የጨረታ አሸናፊው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል:: ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ አይመለስለትም፤ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሃራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል:: ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ በእለቱ ይመለስላቸዋል::
- የሐራጁ አሸናፊ /ገዥ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሊዝን ክፍያን ጨምሮ፣ ግብር፣ በዋጋው ላይ ሚታሰብ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዘዋወሪያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው/አሸናፊው/ ይከፍላል::
- ተጫራቾች በሃራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ (የቀበሌ፣ የመንጃ ፍቃድ፣ ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ) መያዝ ይገባቸዋል:: ተጫራቾች የህግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ህጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሃራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ግለሰብ ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የጸደቀ መመስረቻ ጽሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ ቃለጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት::
- ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል::
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም ከወርካውትና ሪከቨሪ ክፍል ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ጨረታው ከመካሄዱ ከ5 ቀን በፊት መጎብኘት ይችላል::
- ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል:: ነገር ግን ተበዳሪውም ሆነ መያዣ ሰጪው ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል::
- ንብረቱን/ቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም:: ገዥው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል::
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ፣ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ፤ እስከ 100% ድረስ ብድር ሊያመቻች ይችላል::
በንብረቱ ላይ የምርት ተግባር ለሚያከናውኑ ገዥዎች ባንኩ ተጨማሪ ብድር ሊያመቻች ይችላል::
በተጨማሪም ለባንኩ የተሻለ ጥቅም የሚያስገኝ ከሆነ ባንኩ ለመደራደር ዝግጁ ነው:: - የተጫራቾች ምዝገባ ከሃራጁ መዝጊያ ሰአት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል::
- ለበለጠ ማብራሪያ አማራ ባንክ አ.ማ 0115 58 27 64 ወይም 0115-58 41 89 በስራ ሰአት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:
- በወንድ አንቀጽ የተጠቀሰው ለሴት እና ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅትም ያገለግላል::
አማራ ባንክ አ.ማህበር
✨ messages.ai_summary
Amhara Bank re-advertises the auction of a foreclosed residential property on a 249 sq m plot in Tana sub-city, Kebele 16, Bahir Dar, sold as is. The bank may finance up to 100% for qualifying winners.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
