የቡታጅራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በአዋጅ በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሠረት የ2019 1ኛ ዙር የሊዝ ጨረታ በአሬሻ በአረንዛፍ እና ዘቢዳር ቀበሌዎች ለንግድና ኢንቨስትመንት የሚሆን ቦታ በሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል::
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
የቡታጅራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በአዋጅ በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሠረት የ2019 1ኛ ዙር የሊዝ ጨረታ በአሬሻ በአረንዛፍ እና ዘቢዳር ቀበሌዎች ለንግድና ኢንቨስትመንት የሚሆን ቦታ በሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል::
- የጨረታው ዓይነት መደበኛ ጨረታ
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በማዘጋጃ ቤቱ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዘርፍ ቢሮ በመቅረብ ዝርዝር የጨረታ ሰነድ 1000 /አንድ ሺህ/ ብር በመግዛት መወዳደር ይችላሉ::
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለቦታው የሚያቀርቡትን ዋጋ፣ የሚከፍሉትን የሊዝ ቅድም ክፍያ ወይም ለንግድና ኢንቨስትመንት 20% መከፈል የሚችል በጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን የጠቅላላ የቦታው ስፋት በመነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 20 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚጠናቀቀው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 10:00 ሰዓት ሆኖ የጨረታ ሣጥን የሚታሸገው በዕለቱ ከቀኑ 11:00 ይሆናል:: ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡታጅራ ከተማ ሴራና የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 2:30 ሰዓት ይከፈታል::
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ በሁሉም ገጽ ላይ ሙሉ ስማቸውን ፣ ፊርማቸውን፣ የመኖሪያ አድራሻቸውንና ስልካቸውን ማስፈር አለባቸው::
- ጨረታ ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ /ማሻሻያ/ ማድረግና ከጨረታው ራሣቸውን ማግለል አይችሉም::
- ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡትን የጨረታ ዋጋ በአሃዝና በፊደል መግለፅ አለባቸው ሆኖም የአሃዝና የፊደል ልዩነት ካለ በፊደል የተፃፈው ገዢ ይሆናል::
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያቸውን ሞልተው ካስገቡ በኋላ ሰነድ በመሰረዝ በምትኩ ሌላ የጨረታ ሰነድ ማስገባት አይችሉም::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የቅድመ ክፍያ መጠን ከአጠቃላይ የሊዝ ክፍያ 20% ማነስ የለበትም::
- የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በይፋ ከተገለጸ በኋላ በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ /CPO/ ጨረታው ከተፈፀመ በኋላ ካለው የሥራ ቀን ጀምሮ ተመላሽ ይደረጋል፡
- አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ የጨረታ ሰነድ በላይ መግዛት አይችልም::
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ቦታዎች ጨረታው በጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10/አስር/ ቀናት ጠዋት ከ2:30 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ቦታዎችን በመዘዋወር መመልከት ይችላሉ::
- ሌላ ተጫራች በሚሠጠው ዋጋ ላይ በመንተራስ ዋጋ መስጠት አይቻልም::
- በጨረታው ሂደት ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ካልተገኙ የጨረታው ሂደት በሌሉበት የሚከፈት ይሆናል::
- ተጫራቾች ጨረታውን ለማሸነፍ ተገቢ ያልሆነ አድራጐት ከፈፀሙ ወይም የጨረታው ሂደት ለማዛባት ከሞከሩ ከጨረታው የሚታገዱ እና ያስያዙት /CPO/ ለመንግሥት ገቢ እደሚደረግና በአመቱ በሚካሄዱ ጨረታዎች የማይሣተፉ ይሆናል::
- አሸናፊ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በማዘጋጃ ቤቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ከተገለጸበት ቀን ጀምሩ ባሉ ተከታታይ አስር የስራ ቀናት ውስጥ በመቅረብ ያስገባውን ቅድመ ክፍያ በመከፈል ውል መግባት ይኖርበታል::
ማዘጋጃ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
በቡታጅራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በ2019 ዓ.ም. የበጀት ዓመት ለአንደኛ ዙር ለሊዝ ጨረታ ለንግድና ኢንቨስትመንት የቀረቡ ቦታዎች መግለጫ
| ተ.ቁ | ቦታው የሚገኝበት አካባቢ | የቦታው ስፋት በካሬ ሜትር | ቀበሌ | የቀረበ ፕሎት ብዛት | የቦታው ደረጃ | ብሎክና ፕሎት | የቦታው አገልግሎት | የሚገነባው ህንጻ ከፍታ | የጨረታ መነሻ ዋጋ | የሊዝ ዘመን | የጨረታ ዓይነት | የክፍያ ማጠናቀቂያ | የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ |
| 1 | ሀይሌ ወፍጮ ፊት ለፊት | 650 | አረንዛፍ | 1 | 1ኛ | EMB1P1 | ንግድና ኢ/ት | G+4ና በላይ | 1529.30 | 70 | መደበኛ | 40 | 1000.00 |
| 2 | አድማሱ ቶርኖ በስተምስራቅ | 500 | አረንዛፍ | 1 | 1ኛ | ADHP2 | ንግድና ኢ/ት | G+4ና በላይ | 1529.30 | 70 | መደበኛ | 40 | 1000.00 |
| 3 | መስቃን ወረዳ ፖሊስ መግቢያ በስተቀኝ (ፊት ለፊት) | 600 | አረንዛፍ | 1 | 1ኛ | MPP1 | ንግድና ኢ/ት | G+4ና በላይ | 1529.30 | 70 | መደበኛ | 40 | 1000.00 |
| 4 | አሊ አንጩት ቤት ፊት ለፊት ፈረሳት ምግብ ቤት ጎን | 290 | ዘቢዳር | 1 | 1ኛ | DFP1 | ንግድና ኢ/ት | G+4ና በላይ | 1529.30 | 70 | መደበኛ | 40 | 1000.00 |
| 5 | የቀድሞ ዘማር ሆቴል አካባቢ ዴዝሞ ክለብ ፊት ለፊት | 650 | አሬሻ | 1 | 1ኛ | UNB3P1 | ንግድና ኢ/ት | G+4ና በላይ | 1529.30 | 70 | መደበኛ | 40 | 1000.00 |
| 6 | አሜግ ሆቴል በስተምስራቅ አሬሻ ቀበሌ ጎን | 350 | አሬሻ | 1 | 1ኛ | AMBP3 | ንግድና ኢ/ት | G+4ና ላይ | 1529.30 | 70 | መደበኛ | 40 | 1000.00 |
| 7 | መናህሪያ መግቢያ ምንጭ ቁርስ ቤት | 390 | አረንዛፍ | 1 | 1ኛ | BSP1 | ንግድና ኢ/ት | G+6ና በላይ | 1529.30 | 70 | መደበኛ | 40 | 1000.00 |
በቡታጅራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በ2019 ዓ.ም. የበጀት ዓመት ለአንደኛ ዙር ለሊዝ ጨረታ ለንግድና ኢንቨስትመንት የቀረቡ ቦታዎች መግለጫ
| ተ.ቁ | ቦታው የሚገኝበት አካባቢ | የቦታው ስፋት በካሬ ሜትር | ቀበሌ | የቀረበ ፕሎት ብዛት | የቦታው ደረጃ | ብሎክና ፕሎት | የቦታው አገልግሎት | የሚገነባው ህንጻ ከፍታ | የጨረታ መነሻ ዋጋ | የሊዝ ዘመን | የጨረታ ዓይነት | የክፍያ ማጠናቀቂያ | የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ |
| 8 | ቀና ማዘጋጃ አካባቢ አቡጊዳ ጂም ጀርባ | 390 | አረንዛፍ | 1 | 1ኛ | MBP1 | ንግድና ኢ/ት | G+4ና በላይ | 1529.30 | 70 | መደበኛ | 40 | 1000.00 |
| 9 | መስቃን ወረዳ አስተዳደር ፊት ለፊት | 260 | አረንዛፍ | 1 | 1ኛ | MWP1 | ንግድና ኢ/ት | G+6ና በላይ | 1529.30 | 70 | መደበኛ | 40 | 1000.00 |
| 10 | ከሴራና ወደ ንግድ ባንክ መሄጃ በስተግራ | 340 | አረንዛፍ | 1 | 1ኛ | MWP1 | ንግድና ኢ/ት | G+4ና በላይ | 1529.30 | 70 | መደበኛ | 40 | 1000.00 |
| 11 | ከመስቃን ወረዳ ፖሊስ ወደ ሴራና አዳራሽ መሄጃ በስተግራ | 450 | ዘቢዳር | 1 | 1ኛ | MPP2 | ንግድና ኢ/ት | G+4ና በላይ | 1529.30 | 70 | መደበኛ | 40 | 1000.00 |
| 12 | ሳውዘርን ሆቴል ጀርባ | 352 | አሬሻ | 1 | 1ኛ | SH2P1 | ንግድና ኢ/ት | G+4ና በላይ | 1529.30 | 70 | መደበኛ | 40 | 1000.00 |
| 13 | ሳውዘርን ሆቴል ጀርባ | 245 | አሬሻ | 1 | 1ኛ | SH2P1 | ንግድና ኢ/ት | G+4ና በላይ | 1529.30 | 70 | መደበኛ | 40 | 1000.00 |
| 14 | አሜግ ሆቴል በስተደቡብ ህብረት ግሮሰሪ ፊት ለፊት | 600 | አሬሻ | 1 | 1ኛ | AMB2P1 | ንግድና ኢ/ት | G+4ና ላይ | 1529.30 | 70 | መደበኛ | 40 | 1000.00 |
የቡታጅራ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Butajira City Finance Office (Central Ethiopia) offers 14 urban plots of 245 to 650 m² in Arenzaf, Zebidar and Aresha kebeles on 70-year lease by auction for trade and investment use, with G+4 or G+6 and above buildings required. First-round lease auction.
