የሰንበቴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የመኖሪያና የድርጅት ቦታዎች የሊዝ ጨረታ (3ኛ ዙር)
የሰንበቴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
የ3ኛ ዙር የመሬት ሽያጭ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በሰንበቴ ከተማ አስተዳደር የሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በሰንበቴ ከተማ ውስጥ የሚገኙ 11 ቦታዎችን የመኖሪያና የድርጅት ጠቅላላ የቦታው ስፋታቸው 2415 ካሬ ሜትር የሆነውን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል::
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ፍቃድኛ የሆኑ ተጫራቾች :-
- የጨረታውን ሰነድ በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ የኢትዮ. ብር 1000.00 /አንድ ሺ. ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች ቦታው የሚገኝበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታውን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን /Specifection/ መሰረት መሆን ይኖርበታል::
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 30 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ 30 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል::
- ተጫራች የጨረታውን ሰነድ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ በኦ/ብ/ዞን በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ24/02/2019 ዓ.ም እስከ 07/03/2019 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን 07/03/2018 ዓ.ም 11:00 ሰዓት ይሆናል::
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ08/03/2019 ዓ.ም በ4:00 ሰዓት በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- በጋራ ተደራጅተው /በአክሲዮን/ እነ በሚል ሰነድ ለመግዛት የሚፈልጉ አካላት ከሚመለከተው አካል እነ የተባላችሁበትን ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ መረጃ ከነ አባላት ስም ዝርዝር የድርጅቱ ማህተም አርፎበት ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- ቦታውን ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 11:00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በሚመድባቸው አስጎብኝዎች ቦታዎቹን መመልከት ይችላሉ::
- የአካባቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ :-በስልክ ቁጥሮች 0912871993 / 0931969182 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
የሰንበቴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Senbete City Administration Urban and Infrastructure Development Office (Oromo Nationality Zone, Amhara) offers 11 residential and business plots totalling 2,415 m² on lease by auction. Individuals and share-company groups may bid; site visits arranged by the office. Third-round lease auction.
