ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ቦታ እና ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል::
Oromia Bank
ጨረታ ቁጥር: ኦባ/ንአአ/001/2019
ያገለገሉ ዕቃዎች የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019
ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ቦታ እና ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል:: ስለዚህ ዕቃዎቹን መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቦሌ መንገድ ጌቱ ኮሜርሺያል ሴንተር ጎን ከሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.407-8-1 (ከአሴት እና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዋና ክፍል) በመውሰድ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ::
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎች አቃቂ ዩኒቲ አደባባይ አካባቢ (ከአቃቂ ቆርቆሮ ፋብሪካ ጎን) ከሚገኘው የባንኩ መጋዘን በአካል ተገኝተው በማየት ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ሕዳር 03 ቀን 2019 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተገለፀው የባንኩ ዋና መ/ቤት አድራሻ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ::
- ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 8:30 ሰዓት ላይ በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) ሲ.ፒ.ኦ በኦሮሚያ ባንክ አ.ማ. ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው::
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
| ተ.ቁ | የዕቃው ዓይነት | ብዛት |
| 1 | የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዩፒኤሶች (UPS) | 359 |
| 2 | የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ የገንዘብ መቁጠሪያ እና መለያ ማሽኖች | 191 |
| 3 | የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ እስካነሮች እና ፕሪንተሮች | 105 |
| 4 | የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ የፎቶ ኮፒና የፋክስ ማሽኖች | 60 |
| 5 | ያገለገሉ የኤሌክትሪክ የሂሳብ ማሽኖች | 60 |
| 6 | የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዴስክ ቶፕ ኮምፒዩተሮች | 38 |
| 7 | ያገለገሉ የዩፒኤስ ባትሪዎች (UPS Battery) | 45 |
| 8 | ከብረት የተሰሩ ያገለገሉ የገንዘብ ማስቀመጫ ሳጥኖች | 36 |
| 9 | ያገለገሉ የኔት ዎርክ ሲስኮ ራውተር፣ ዲ-ሊንክ፣ 3-ኮም | 10 |
| 10 | ያገለገሉ የመተይቢያ ማሽኖች (Type Writers} | 11 |
| 11 | የተለያዩ ያገለገሉ እስታብላይዘር (Gato) ፣ የዉኃ ማጣሪያ ፣ እና ቬንትሌተር | 06 |
| 12 | የተለያዩ ያገለገሉ ዲጂታል የፎቶ ካሜራዎች | 07 |
| 13 | የተለያዩ መጠን ያላቸዉ ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎች | 120 |
| 14 | የተለያዩ ያገለገሉ ስብርባሪ ወይም ቁርጥራጭ ብረታ-ብረቶች | ባለበት |
| 15 | የተለያዩ ያገለገሉ ተንቀሳቃሽ፣ ስብርባሪ መስታወቶች ወይም የፋይበር ግላሶች | ባለበት |
| 16 | ከባንኩ ቅርንጫፎች የተነሱ የተለያዩ መጠን ያላቸዉ ያገለገሉ ካውንተሮች | ባለበት |
| 17 | የተለያዩ ያገለገሉ የተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎች (Used Spare Parts) | ባለበት |
መደበኛ ስልክ ቁጥር:- 0115-57-20-37 0114-62-49-19 ተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥር:- 0912-73-64-32
0913-46-99-87/0911-69-53-48
ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ
✨ messages.ai_summary
Oromia Bank sells used items as is, viewable at its Akaki warehouse: UPS units and batteries, money counting and detecting machines, scanners, printers, photocopiers, fax machines, calculators, desktop computers, safes, routers, typewriters, cameras, vehicle tyres, scrap metal and spare parts.
