Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline25 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityእያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል::
  • opening dateየቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል:: የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale , Automotive Materials

ሐራጅ ማስታወቂያ – የSTARA 2021 ሞዴል ተሽከርካሪ ሽያጭ በፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ መሠረት በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ የሚገኝ የሰሌዳ ቁጥር 3-B69195 የሆነ የ2021 ሞዴል STARA ተሽከርካሪ በ5,273,506 ብር መነሻ ዋጋ ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የትራንዛክሽን ታክስ በገዥ ይከፈላል።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ሙሪድ ነከር እና የፍ/ባለዕዳ ያሲን አብደላ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/325507 በ14/05/2017ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ.335740 በቀን 21/09/2017ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ.335740 በቀን 20/10/2017ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ግቢ ውስጥ ቆሞ የሚገኝ የሰ/ቁ.ኮድ 3-B69195 አ.አ የምርት ዘመኑ 2021 የሆነ ስታሪያ( STARA) ተሽከርካሪ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 5,273,506 (አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰባ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ስድስት) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 16 ቀን 2019ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል:: የተጫራቾች ምዝገባ 8:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል::የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል:: ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CP.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::

በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Federal Courts Judgment Enforcement Office auctions, by court order, a 2021 Staria (STARA) vehicle parked at the Rehoboth parking lot, Woreda 06, Kolfe Keranio sub-city, Addis Ababa.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender