ሐራጅ ማስታወቂያ – የፔጆ 504SR ተሽከርካሪ ሽያጭ በፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ መሠረት በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ የሚገኝ ኮድ 2-37126 አ.አ የሰሌዳ ቁጥር ያለው ፔጆ 504SR ተሽከርካሪ በ157,440 ብር መነሻ ዋጋ ህዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የትራንዛክሽን ታክስ በገዥ ይከፈላል።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ዘይነብ ያህያ እና የፍ/ባለዕዳ አቶ ሙላታ ኑር ሁሴን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 106960በ5/2/2017 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ/114322 በ30/03/2017 ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/114322 በ08/10/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ግቢ ውስጥ ቆሞ የሚገኝ የሰ/ቁ. ኮድ 2-37126 አ.አ ሞዴል 504SR Peejo ( ፔጆ ) ተሽከርካሪ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 157,440 (አንድ መቶ ሃምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ አርባ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 14 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል:: የተጫራቾች ምዝገባ 8:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል:: 2ኛ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 073/07 ውስጥ የሚገኙ ፍ/ያረፈባቸው ያገለገሉ ንብረቶች (ላፕቶፕ ፎቶ ኮፒ ፋክስ ማሽን ተሽከርካሪ ወንበር....) የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 87,584 (ሰማንያ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ አራት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 14 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል:: የተጫራቾች ምዝገባ 8:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል:: የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን ፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል:: ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም:: በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን ፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +25112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::
