ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር የኮምፒውተርና ተዛማች እቃዎች ግዥ
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር EAC 002/2019
- ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የኮምፒውተር እና ተዛማች እቃዎች ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2:30 - 6:30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7:30 -11:00 ድረስ "ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት አንድ ዋና /Original የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጎ እንዲሁም፤ አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ታሽጎ ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት:: በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል:: ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም:: የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል::
- ተጫራቾች የ ኮምፒውተር እና ተዛማች እቃዎች ግዥ የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (Unconditional) ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ በ4:30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፣ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተዘግቶ 4:45 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ይሆናል::
- ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን::
- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09-11-93-73-75 መጠቀም ይችላሉ::
- ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር
✨ messages.ai_summary
Ethio Agri-CEFT PLC (MIDROC Investment Group) seeks suppliers of computers and related accessories. Bidders need a renewed trade licence, TIN, tax clearance, supplier list registration and VAT certificate. Open bid.
