Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline23 Nov 2026, 10:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Security1/4ኛ ብር 700,000 (ሰባት መቶ ሺህ ብር)
  • opening dateህዳር 14 ቀን 2019ዓ/ም
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የፍርድ አፈጻጸም ሁለተኛ ዙር ሐራጅ ማስታወቂያ፡ በኮ/ቀ/ክ/ከ ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ግቢ የሚገኝ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-47338 ኦሮ ዶልፊን የሕዝብ ተሽከርካሪ በ2,800,000 ብር መነሻ ዋጋ ለሐራጅ ይቀርባል። የትራንዛክሽን ታክስ በገዥ ይከፈላል።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት አልማዝ ወርቁ እና የፍ/ባለዕዳ ጌታመሳይ ግርማ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/214677 ሰኔ 27 ቀን 2017 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/274048 በ14/05/2018ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/274048 በ18/07/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ክ/ከ ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ግቢ ውስጥ ቆሞ የሚገኝ የሰ/ቁ ኮድ 3-47338 ኦሮ ዶልፊን የሕዝብ ተሽከርካሪ የሐራጅ መነሻ ዋጋ 2,800,000 (ሁለት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺህ) ሆኖ የትራንዝክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡

ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.274048 በ10/02/2019 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በድጋሚ ሐራጅ ጨረታ ሆኖ 1/4ኛ ብር 700,000 (ሰባት መቶ ሺህ ብር) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራንዝክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 14 ቀን 2019ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ cP.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን ፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +25112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፌዴራል ፍ/ቤት የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
A public transport vehicle (Oro Dolphin, plate code 3-47338) is being sold at auction by the Federal Courts' execution office, located at Robobot parking yard, Woreda 06. Transaction tax is paid by the buyer. Bidders must deposit 1/4 of the starting price via CPO; the winner must pay the full amount within 15 days.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender