Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
  • Address ኮተቤ ብረታ ብረት መሣሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-42-95
  • Websitehttps://www.eep.com.et/?lang=am
  • Deadline13 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት ወይም ደግሞ በኦላይን አክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ሲ.ፒ.ኦ. በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ እንደሚከተለው አቅርቧል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር /EEP /DS/03/19

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ እንደሚከተለው አቅርቧል፡፡

ሎት 1 ለተለያዩ አገልግሎቶች ሊውሉ የሚችሉ አገልግሎት የሰጡ ሰባት (7) ተሽከርካሪዎች ኮተቤ አካባቢ ብረታ ብረት ፊት ለፊት የሚገኘው ተቋማችን ዋና መ/ቤት ቅጥር ግቢ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፤

ማሳሰቢያ ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ማላይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www. auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን “መስፈርቶቹም ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

  1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሠ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
  2. ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ በነጻ አውርደው መመልከት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ማስታወቂያ ከወጣበት ከሰባተኛው ቀን ጀምሮ አክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ጋር ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 እስከ 10:00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት የተቋሙ ጣቢያዎች በመገኘት መመልከት ይቻላል፤
  4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት ወይም ደግሞ በኦላይን አክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ሲ.ፒ.ኦ. በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
  6. ጨረታው ከ20/02/2019 እስከ 04/03/2019 ዓ.ም እስከ ጠዋት 4:00 ድረስ ይካሄዳል ስለሆነም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታዉን ሂደት በቀጥታ (online) መከታተል ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
  8. በጨረታው አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ለወደፊት አሸናፊነታችሁ በሚገለፅላችሁ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀኖች ውስጥ የአሸነፋችሁበትን ዋጋ ሙሉውን ክፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ በተቋማችን ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት መፈጸም ግዴታ ይኖርባችኋል፤ ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ለወድድር ያስያዛችሁት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ለተቋማችን ገቢ ይደረጋል፤
  9. ከላይ የተጠቀሰውን እና በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ/ሊሰረዝ ይችላል፤
  10. ተቋሙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
  11. የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-5511/ 011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  12. ንብረቶቹን በተመለከተ በስልክ ቁጥር 011-558-14-24 ወይም 011-558-06-49 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Electric Power is selling used service vehicles (Lot 1: seven vehicles) on an as-is, where-is basis via national open auction, conducted only through the Auction Ethiopia app/website. Open to legally qualified Ethiopian bidders with proof of citizenship or renewed ID.
Not stated in the notice: opening date, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender