Tender Detail

Tender Details

  • Company Modjo Customs Branch Office (የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
  • Address ሞጆ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0222369094
  • Website
  • Deadline06 Nov 2026, 11:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceበአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም (online)
  • Bid Securityየሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 5% (CPO)
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure

የተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች ግልፅ ጨረታ ሽያጭ (Air Compressor፣ አልባሳት፣ ጫማ፣ ሽቶ፣ Passenger Lift እና ሌሎች፣ ግ11/2010) - በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

Modjo Customs Branch Office (የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)


የተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች ግልፅ ጨረታ
ቁጥር ግ11/2010 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 መሰረት የተተዉ ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን በአቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀፅ 9 መሰረት የተተዉና የተወረሱ ንብረቶችን ማለትም Air compressor፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ ሽቶዎች፣ ፑርሞገ፣ ቻርጀር፣ CASTROL oLi ፣Hair stralghtener፣እና ሌሎች እቃዎች፣ Passenger Lift እና Umbrella እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ ከአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በመግዛት ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ሲሆን አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ከአክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሰነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶችን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2:00 እስከ ቀኑ 6:00 ሰአት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7:00 እስከ ቀኑ 10:30 ሰአት እና ዓርብ ከጠዋት 2:00 እስከ ቀኑ 5:00 ሰአት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7:30 እስከ ቀኑ 10:30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2:00 እስከ ቀኑ 5:30 መመልከት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነዱን ከአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም /ድረገፅ/ አንላይን ላይ ብቻ መግዛት እና መጫረት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ በአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ማያያዝ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሥም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ፣አዳማ እና ሞጆ ቅርንጫፎች ብቻ አሰርተው አክሽን ኢትዮጵያ ሄደው በማስያዝ ወይም በአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ባለው የሲፒኦ አማራጮች አንላይን ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አስቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን፤ ዕቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፣ በጨረታ ተሸጦ የተወሰደ እቃ ተመላሽአይደረግም፡፡ ለእቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም፡፡
  6. ተጫራቾች የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 8ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 5:00 ሰአት ድረስ በአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም መወዳደሪያ ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደትና ውጤት አንላይን መከታተል ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ 15% ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  9. ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታ ከተጀመረ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፤ በጨረታ ሽያጭ ውድድር ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታው ተጀምሮ ዋጋ ከሰጡ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይቻልም ፡፡ የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  10. የግልጽ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት፡፡ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
  11. በተራ ቁጥር 10 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳ/ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል፡፡ ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል፡፡
  12. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።
  13. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ ያቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው፡፡ በጨረታ ተሸጦ በጨረታ አሸናፊው የተወሰደ እቃ አይመለስም፡፡
  14. የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር ስልክ ቁጥር መስመር 9164 ወይም 09-05-11-55-11/011-666-8828 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
  15. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 022-236-90-94 /022-236-01-90 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Modjo Customs Branch Office is selling abandoned and confiscated goods by open bid, including an air compressor, clothing, shoes, perfume, a passenger lift, and other items. Bidders must hold a valid trade license, TIN, and VAT registration, and must inspect the goods before bidding. Bidding is online only via the Auction Ethiopia platform.
Not stated in the notice: opening date. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender